መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነቡ የኃይል ማመንጫ ግድቦች በታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ላይ ተጽዕኖ ቢኖራቸውም፣ በትብብር ከተመሩ ለቀጠናው ትልቅ ጥቅም እንደሚሰጡ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ኢንጅነር ጌዲዮን አስፋው ገልጸዋል። ውሳኔው የኢትዮጵያን ሀገራዊ የኃይል አቅርቦት ለማስፋፋት፣ የኤሌክትሪክ ተዳራሽነትን ለማረጋገጥ እና ትርፍ ኃይልን ለጎረቤት ሀገራት በመሸጥ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ይናገራሉ። ደቡብ ሱዳን በላይኛው ናይል ተፋሰስ ላይ ግድብ ለመገንባት የምታደርገው እንቅስቃሴ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን (CFA) መሠረት ያደረገ መሆኑን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪ አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ ተናግረዋል፡፡ ውሳኔው እስካሁን በግብፅ በኩል የነበረውን የውኃ አጠቃቀም የበላይነትና ጫና በጋራ ለመጋራት እንዲሁም ፍትሐዊ አጠቃቀምን ለማስፈን ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል። ለኢትዮጵያ በዲፕሎማሲና በልማት ዘርፍ ድጋፍ የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ፣ ሌሎች የተፋሰሱ ሀገራትም ወደ ተመሳሳይ የልማት እንቅስቃሴዎች እንዲገቡ መንገድ የሚከፍት በመሆኑ ለቀጠናው ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት የወሰደችው ውሳኔ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚያስጠብቅና የተፈጥሮ ሀብቷን የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን የሚያረጋግጥ መሆኑን የዲፕሎማሲ ባለሙያው አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ገልጸዋል። ውሳኔው ከኢትዮጵያም ሆነ ከሌሎች የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት የጋራ ስምምነት ጋር የሚጣጣም መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ፤ ግድቡ መገንባቱ ሀገራት የተፈጥሮ ሀብታቸውን በሉዓላዊነት የመጠቀም መብታቸውን የሚያጠናክር እና የጋራ ተጠቃሚነት መርሕን የሚያጎለብት ነው ብለዋል። የግድቡ መገንባት የደቡብ ሱዳንን ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ባለፈ፣ ሌሎች የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትንም በጋራ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ተመላክቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ኢትዮ ቴሌኮም በቀጣዩ ዓመት ለ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ማቀዱን አስታወቀ
ነሐሴ 28 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮ ቴሌኮም "NEXT Horizon - Year 2" በሚል የ2018/19 በጀት ዓመት ዕቅዱን ይፋ አድርጓል። በዚህም... read more
የትራንስፖርት አገልግሎቱ ላይ የሚነሱ አጠቃላይ ችግሮችን ለመቅረፍ የሰው ሃይል እጥረት እንዳለበት ቢሮዉ ገለጸ
ኅዳር 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቂ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ብቁ የሰው ሃይል እንደሌለዉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
አሁን... read more
የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት የዚህ አመት ምዝገባ እስከ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ተገለጸ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፀዳለ ተክሉ የዚህ ዓመት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ምዝገባ... read more
ከአሜሪካ ምዕራብ ወደ ምሥራቅ የሚያሻግረው ታሪካዊ የባቡር ጉዞ
ሕዳር 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአሜሪካን አህጉር ከምዕራብ ዳርቻ (ፓሲፊክ ውቅያኖስ) ወደ ምሥራቅ ዳርቻ (አትላንቲክ ውቅያኖስ) የሚያገናኘው አስደናቂ የባቡር ጉዞ ርዝመትና... read more
1ሺህ 500 የሚሆኑ እና ከአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ዜጎች ተሳታፊ የሚሆኑበት 3ኛው የስራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ሊካሄድ እንደሆነ ተገለጸ
ሰኔ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ ካላት እምቅ የሰው ሀይል መካከል ወጣት ክፍሉ ይገኝበታል ያለው የኢፌድሪ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ነው።
የሚኒስቴር... read more
በጀርመን በግድግዳ ላይ ሽንት ለሚሸኑ ሰዎች ያልተጠበቀ ቅጣት ተዘጋጀ
ነሐሴ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጀርመኗ የሃምቡርግ ከተማ፣ በተለይም በምሽት ህይወቷ ለምትታወቀው ለስትሪት ፓውሊ ወረዳ፣ አዲስና እጅግ አስገራሚ የሆነ የንፅህና... read more
ወንዶች በዓመት 7 ሰዓት በመታጠቢያ ቤት ውስጥ ያሳልፋሉ ተባለ
ነሐሴ 08 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) አዲስ የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ወንዶች በዓመት በአማካይ ሰባት ሰዓታትን የሚጠቀሙት በመታጠቢያ ቤት ውስጥ ነው፤... read more
ላሚን ያማል ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ መሆኑ ተረጋገጠ
ሕዳር 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የስፔን ብሔራዊ ቡድን እና የባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ በላሚን ያማል ጉዳይ የገቡበት ውዝግብና አለመግባባት እንደቀጠለ... read more
የአርበኞች ቀንና የኋላ ታሪካቸው
👉
https://youtu.be/8PGo7h-L6zU
read more
ምላሽ ይስጡ