መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በመጪው መስከረም 16 ቀን 2019 የሚከበረው የደመራ እንዲሁም የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር ቢሮው የሰላምና ፀጥታ ሥራውን እየሠራ እንደሚገኝ ለጣቢያችን አስታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሥሐ ጥበቡ፤ በዩኔስኮ የተመዘገበው የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር የፀጥታ አካላት በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። አስቀድሞ ከማህበረሰቡ ጋር በቂ ውይይት መደረጉን የተናገሩት አቶ ፍሥሐ፤ የኢትዮጵያን ገጽታ ሊገነባ በሚችል ደረጃ በዓሉ እንዲከበር ከፀጥታ አኳያ ተገቢው ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል። ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለውም የሃይማኖት አባቶች በሚያስቀምጡት ሥርዓት መሠረት በዓሉ እንዲከበር ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ አሳስበዋል። ከፀጥታ ጎን ለጎን በየሰፈሩ በሚካሄደው የደመራ ማብራት ሥርዓት ላይ ምንም ዓይነት አደጋ እንዳይከሰት ተገቢው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በዚህ በዓል ላይ በርካታ የሀገር ውስጥ እንዲሁም ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ቱሪስቶች የሚገኙ በመሆኑ፣ የፀጥታ አካላት አስቀድመው ሕግና ሥርዓትን በጠበቀ መልኩ የፍተሻ እና የቅኝት ሥራዎችን እንደሚያደርጉ አመላክተዋል። መስቀል እንዲሁም በቀጣይ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተገቢውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የአሜሪካው ኤፍ-15 ጄት በኢራን ሰማይ ላይ ከመውደቁ በፊት ያጋጠመው አስገራሚ ክስተት፤ “የጄሊፊሽ ቅርጽ ያላቸው ድሮኖች ከበቡን”
ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በቅርቡ በኢራን የአየር ክልል ውስጥ የተመታው የአሜሪካ አየር ኃይል ኤፍ-15 ኢ ስትራይክ ኢግል ተዋጊ ጄት ፓይለት... read more
በዝናብ ወቅት የሚከሰት የዶሮ በሽታን ለመከላከል መንግስት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የዝናብ ወቅት ለዶሮ በሽታ አምጪ ተህዋስያን መራባትና መስፋፋት አመቺ በመሆኑ፣ መንግስት የባለሙያ ድጋፍና የግንዛቤ ማስጨበጫ... read more
በትግራይ ከሚካሄደዉ የምክክር ሂደት በፊት ልዩ ዉይይት ከወጣቶች ጋር እንደሚኖር ተጠቆመ
ሰኔ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል የሚካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የምክክር ሂደት ከመጀመሩ አስቀድሞ ከክልሉ ወጣቶች ጋር ልዩ የውይይት... read more
ትኩረት ያልተሰጠው ፓርኪንሰንስ ህመም እንዴት ይከሰታል? 👉
https://youtu.be/070xgt5tVhk
read more
በታክስ ስወራ፣ የተጨማሪ ታክስ አለመክፈል፣ በኮንቶሮባንድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተከሰሱ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በታክስ ስወራ፣ የተጨማሪ ታክስ አለመክፈል፣ በኮንቶሮባንድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል... read more
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የልምድ ልውውጥ መርሐ-ግብር ነገ ያካሂዳሉ
ሚያዚያ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት... read more
ከሰሞኑን በጸደቀው አዋጅ 1387/2017 መሰረት የሚደረገው ምርመራ ከመደበኛው የወንጀል ምርመራ ሂደት በተለየ ዘዴ መሆኑ ተገለጸ
ሰኔ 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የቀድሞውን አዋጅ 780/2005ን ለማሻሻል የወጣው እና ሰኔ 10/2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው አዋጅ 1387/2017... read more
28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተጭበርበሩ
28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መጭበርበራቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ የገንዘብ ደህንነት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡
የባንኩ ሪፖርት... read more
አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት የንግድ ጦርነትን በ15 በመቶ ታሪፍ እንዲሆን ተስማሙ
ሐምሌ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት ለረዥም ጊዜ ሲያስጨንቅ የነበረውን የንግድ ጦርነት ለማስቀረት የሚያስችል ታሪፍ ስምምነት... read more
የኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ሥራ ማኅበር ለሴቶች የተሻሉ የብድር አማራጮችን ይፋ አደረገ
ሰኔ 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዋጅ ቁጥር 985/09 መሠረት በ2017 ዓ.ም የተቋቋመው ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ሥራ ማኅበር፣ ለሴቶች... read more
ምላሽ ይስጡ