መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኤሊኖን ለዘመናት በተለያየ ስያሜ እየተጠራ አሉታዊ ተጽዕኖ ሲያሳድር የቆየ አለም አቀፍ ክስተት እንደሆነ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የስትራቴጂክና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አይድሩስ ሀሰን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሜትሪዮሎጂ ኢንስቲትዮት በሰጠው የትንበያ መረጃ፣ በአገሪቱ በ8 ክልሎች፣ በ37 ዞኖች፣ በ178 ወረዳዎች የኤሊኖን ክስተት እንደሚያጋጥም መገለጹን አስታውሰዋል። ዘንድሮ በተከሰተው ኤሊኖን ሁለት ከፍተኛ ተጽዕኖዎች ማለትም ከፍተኛ የዝናብ እጥረት ወይም ድርቅ እና የጎርፍ አደጋ እንደሚጠበቅ ምክትል ኮምሽነሩ አመላክተዋል። ኮምሽኑ ከሌሎች የመንግስት ተቋማት ጋር በመሆን ለክስተቱ ብቻ ሳይሆን ከኤሊኖን ባሻገር ምላሽ ለመስጠት በቂ ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል። ክስተቱን ተከትሎ ለሚያጋጥም አደጋ ምላሽ ለመስጠት የሰብዓዊ እርዳታን በራስ አቅም ለመሸፈን ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በሰጡት አቅጣጫ መሰረት በተጀመረው “የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” ትልቅ አቅም መፍጠር እንደተቻለ አመላክተዋል። በዚህም መሰረት እንደ አገር ለኤሊኖን ብቻ ሳይሆን፣ ከኤሊኖን ባሻገር ለሚያጋጥም አደጋ ምላሽ ለመስጠት በቂ ዝግጅት እንደተደረገ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የስትራቴጂክና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አይድሩስ ሀሰን አስታውቀዋል። ኮምሽኑ ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ጋር በጋራ ባዘጋጀው መድረክ ለፌደራል እና የክልል የኮምዩኒኬሽን እና ሚዲያ አካላት በኤሊኖን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት እና በተቀናጀ የሚዲያ እና መረጃ ልውውጥ ዙሪያ ምክክር እያደረገ ነው። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በመስቀል ዋዜማ 19 የጉራጌ ዞን መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚው በአቶ አንዋር አብራር በኩል ባወጣው ይፋዊ የሚዲያ... read more
የ2017 ጳጉሜ ወር ቀናት ስያሜን መንግስት ይፋ አደረገ
ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባለፉት 6 ዓመታት የጳጉሜ ወር ቀናት ስያሜ ተሰጥቶት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲከበር የቆየ ሲሆን፣ የ2017... read more
🛑 ሰበር የህክምና ዜና፡ በሰው ግንባር ላይ የበቀለው አስደናቂው አፍንጫ!
መጋቢት 16 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በከባድ ኢንፌክሽን ምክንያት አፍንጫቸውን ላጣ ግለሰብ የተደረገው የህክምና ተዓምር በመላው ዓለም መነጋገሪያ ሆኗል።
የዘመናዊ ቀዶ ጥገና... read more
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የብስክሌት ትራንስፖርትን ለማስፋፋት የአሰራር ደንብ እንዲፀድቅ ጥያቄ ማቅረቡን ገለጸ
ታኅሳስ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የብስክሌት ትራንስፖርት ለማስፋፋት የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ... read more
የሽንት ቤት ወረቀት ለማግኘት ማስታወቂያ መመልከት ግዴታ ሆነ
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በቻይና አንዳንድ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች፣ የሽንት ቤት ወረቀትን ለመስጠት ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠ አዲስ ሥርዓት መዘርጋታቸው... read more
ያለ ረዳት በሚሰሩ የታክሲ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ቢሆንም አሁንም ክፍተቱ እንዳለ ነው ተባለ
ሐምሌ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ "ሚኒባስ" ታክሲዎች ያለ ረዳት መንቀሳቀስ እንደማይችሉ እና ተሳፋሪን... read more
በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በደብረብርሃን ከተማ በእሳት አደጋ የአንድ የቤተሰብ አባላት የሆኑ ሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል ተባለ
በተጨማሪም በሐረር ከተማ ዛሬ ሌሊት 8፡00 ሰዓት ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል ነው የተባለው
በደብረ ብርሀን ከተማ በደረሰ... read more
በኢትዮጵያ የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች የመንገድ ላይ ደህንነት ከጊዜያዉ መፍትሄ ዉጭ ትኩረት እንደተነፈገዉ ተገለጸ
የአሽከርካሪዎች ግድያ፣ ዝርፊያና እንግልት እንዲሁም እገታ እየተባባሰ በመምጣቱ አሽከርካሪዎች ስራቸውን ለማቆም ሊገደዱ እንደሚችሉ ስጋት እንዳለው የኢትዮጵያ ከባድ ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች ማህበር... read more
ስዊዘርላንድ ከአሜሪካ ጋር የገባችውን የፓትሪዮት ሚሳኤል ስምምነት ልታቋርጥ እንደምትችል አስጠነቀቀች
መጋቢት 24 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአውሮፓዊቷ ሀገር ስዊዘርላንድ እና በአሜሪካ መካከል ያለው የቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ግዢ ስምምነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ... read more
ከሰል የማክሰል ሂደቱ በሳይንሳዊ መልኩ ባለመደገፉ ተፈጥሯዊ የአደጋ ስጋቶች እየጨመሩ መሆኑ ተገለጸ
ኢትዮጵያ የከሰል ምርትን በስፋት ከሚጠቀሙ 5 ሀገራት አንዱዋ ስትሆን ምርቱን ለአለም አቀፍ ገበያ በከፍተኛ ደረጃ በማቅረብ የሚታወቁ 5 ሀገራት እንዳሉም... read more
ምላሽ ይስጡ