መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም. (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ግብርና ፅህፈት ቤት በቀጠናው አጥፊው የግሪሳ ወፍ መከሰቱን አስታወቀ። ፅህፈት ቤቱ ወረርሽኙን በአጭር ጊዜ ለመግታትና በሰብል ላይ የሚያደርሰውን ውድመት ለመከላከል ያለመ አስቸኳይ የኬሚካል ርጭት ዘመቻ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ነገ የሚቀጥል መሆኑን ገልጿል። በዚሁ መሠረት የመከላከያ ርጭቱ ዛሬ ምሽት ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ የሚከናወን ሲሆን፣ ርጭቱ በሚካሄድባቸው ቦታዎች ላይ ኬሚካሉ ለጤና አደገኛ ሊሆን ስለሚችል አካባቢዎቹ ከሰውም ሆነ ከእንስሳት ንክኪ ሙሉ በሙሉ ነፃ መደረግ እንዳለባቸው ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። በተጨማሪም ዘመቻው የተሳካ ይሆን ዘንድ ህብረተሰቡ ከግብርና ባለሙያዎች ጎን በመቆም ወፎቹ የሚያድሩበትን ትክክለኛ ቦታ በመለየት፣ መረጃ በመስጠትና አሰሳ በማድረግ ንቁ ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ተ አስተላልፏል። የአካባቢውን ግብርና ከጥፋት ለመታደግ ከተማ አስተዳደሩ ያስተላለፈውን ይህንን አጣዳፊ መረጃ ነዋሪዎች እርስ በርሳቸው በማጋራትና ላልሰሙት በማድረስ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ተጠይቋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ለጋዜጠኞች የሙያ ማረጋገጫ እውቅና አልሰጥም – የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን
መጋቢት 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት፤ ለጋዜጠኞች የሙያ ማረጋገጫ ለመስጠት እና የጋዜጠኞች ምዝገባ ለማከናወን ውይይት እና እንቅስቃሴ... read more
የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ 1.5 ሚሊየን የሚጠጉ ጎብኚዎች ወደ ላሊበላ ከተማ ያቀናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ
ታኅሳስ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዚህ ባለንበት ወርሃ ታህሳስ መጨረሻ ላይ የሚከበረዉን የገና በዓል በስፋት ከሚከበርባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ የላሊበላ... read more
በካናዳ ቅዝቃዜውን የሚያቀልሉ ‘የልብስ ደኖች’፡ ለችግረኞች የሚቀርብ ልብ የሚነካ የሙቀት ስጦታ
መስከረም 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በካናዳ በክረምቱ ወቅት ሰዎችን ከብርድ ለመጠበቅ ያለመ “የልብስ ደኖች” የሚል ልብ የሚነካ ሰብአዊ ተነሳሽነት በመላ... read more
ኢትዮጵያ ታሪኳን በአግባቡ መሰነድ ያለመቻሏ ምክንያት ምንድነው?
https://youtu.be/IlFirzEtWHk?si=bEJIMRBlYUUxWNYJ
read more
በቅርቡ ለቁጥጥር አመቺ የሆነ ዘመናዊ አሰራር ተግባራዊ እንደሚደረግ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ገለጸ
ጥር 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ጉባዔ የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የተዘጋጀውን... read more
ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለትግራይ ልማት ማህበር የተሰጠ ማሳሰቢያ
ሙሉ መግለጫው ከታች ተያይዟል
ጉዳዩ፡ ማህበሩ በቅርቡ ያካሄደው ጉባኤን ይመለከታል
የትግራይ ልማት ማህበር (ትልማ) በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በመዝገብ... read more
“ፎቶዬ አላማረኝም!” – ተፈላጊ ወንጀለኛ ለፖሊስ ‘ሰልፊ’ ልኮ ራሱን አሳልፎ ሰጠ
👉ወንጀለኛው በፖሊስ እየተፈለገ ፖሊስ የለጠፈውን ፎቶ ሲመለከት "ፎቶዬ አያምርም" ብሎ ሌላ የሰልፊ ፎቶ አንስቶ ለፖሊስ በመላኩ በቁጥጥር ስር ውሏል ነው... read more
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ለአማራ ክልል ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የምግብ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ
ታኅሳስ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በአማራ ክልል በተከሰተው ድርቅ የከፋ ችግር ላይ ለሚገኙ ዜጎች ከ5 ሚሊዮን ብር... read more
ኦይል ሊቢያ እና ቶታል ኢነርጂስ፤ አሽከርካሪዎች ባሉበት ሆነው ወረፋ መያዝ የሚችሉበትን አሰራር መዘርጋታቸው ተገለጸ
ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ነዳጅ ለመቅዳት በርካታ አሽከርካሪዎች ረጃጅም ሰልፎችን መጠበቅ እየተለመደ መጥቷል በመላት ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡ ይህን እንግልት... read more
“በጸጥታና ደህንነት ተቋማት ያከናወነው የሪፎርም ስራ ኢትዮጽያን የሚመጥንና ዘመን ተሻጋሪ ተቋማትን ለመገንባት ጠንካራ መሰረት የጣለ ነው። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ደግሞ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ነው። አየር ኃይሉ 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ባለበት በዚህ ወቅት ”ጸሐይ 2 ” የተሰኘችና በአየር ኃይሉ የተሰራች አውሮፕላን ለበረራ ብቁ አድርጓል። አውሮፕላኗ ግዳጅን በብቃት መፈጸም የሚያስችል ቴክኖሎጂ የታጠቀች ናት። ይህም አየር ኃይሉ በ2030 በአፍሪካ ስመጥር አየር ኃይል ለመሆን የያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ በትክክለኛ ጎዳና ላይ መሆኑን የሚያመላክት ነው።” 👉ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ
__
ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን... read more
ምላሽ ይስጡ