መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሚቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያለፈውን የክረምት ወቅት የአየር ጠባይ ግምገማ እና የበጋ ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ይፋ የሚደረግበት መድረክ በዛሬው ዕለት አካሂዷል። ግምገማው የትንበያ ጥራትን፣ ተደራሽነትንና ተጠቃሚነትን ለማሻሻል የሚያግዙ አቅጣጫዎችን ለመለየት እድል የሚፈጥር በመሆኑ፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ሁኔታዎችን ቀድሞ ግንዛቤ እንዲኖር በማድረግ ተገቢ ዝግጅትና የምላሽ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት የገለጹት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እና በዓለም ሚቴዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፈጠነ ተሾመ ናቸው። በመድረኩ የ2018 ክረምት ወራት የዝናብ ስርጭት እና የነበሩ ተጽዕኖዎች፣ እንዲሁም የ2019 የበጋ የአየር ሁኔታ ትንበያ ይፋ ተድርጓል። በአብዛኛው የሀገሪቱ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከመደበኛ በላይ እንደሚሆን የኢንስቲትዩቱ የትንበያ መረጃ ጠቅሷል። ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን ተነስቷል። በአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች በበጋ ወቅት የሚከናወኑ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል። የውሃ አቅርቦትን ከማሻሻል አንጻርም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል። በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ስፍራዎች ላይ የሚጥለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሚሰበሰቡ እና በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችልም ተጠቁሟል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በአሜሪካ ላሞች ላይ የVR መነጽር በማድረግ ጭንቀታቸው እንዲቀንስ እየተደረገ ነው ተባለ
👉መነጸሩ አረንጓዴ ሜዳዎችን እንዲያዩና ብዙ ወተት እንዲያመርቱ ያግዛቸዋል ነው የተባለው
ነሐሴ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ በሚገኙ አንዳንድ እርሻዎች ላሞች በረት... read more
አስትሮይድ በ2032 ጨረቃን ሊመታ ይችላል
👉የምድር ሳተላይቶችም ሊጎዱ ይችላሉ ተባለ
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ቀደም ሲል ምድርን ሊመታ ይችላል ተብሎ ሲሰጋ የነበረው አስትሮይድ 2024 YR4፣ አሁን... read more
በጋምቤላ ክልል የሙቀት መጠን እየጨመረ በመምጣቱ ከነገ ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚቆይ የስራ ሰዓት ለውጥ እንደሚደረግ ታውቋል
በጋምቤላ ክልል የሙቀት መጠን እየጨመረ በመምጣቱ የመንግስት የስራ ሰዓት ከነገ ጀምሮ ለውጥ እንደሚደረግ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አስታውቋል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር... read more
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሰራተኞችን ስራ ለማቆየት ደመወዛቸውን ቀንሰው ከፓይለቶች ያነሰ ገቢ እንዲያገኙ ማድረጋቸው ተገለጸ
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጃፓን አየር መንገድ (Japan Airlines - JAL) ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ሃሩካ ኒሺማትሱ፣ የኩባንያውን ሰራተኞች... read more
በመዲናዋ እየተካሄደ ያለው 13ኛው የአፍሪካ ኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ከኢንተርኔት አጠቃቀምና ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ለሚወጡ ህጎች አጋዥ እንደሚሆን ተገለጸ
ኅዳር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለመጀመሪያ ጊዜ በሃገራችን እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ከተለያዩ ሃገራት የተወጣጡና በዘርፉ ያሉ ባለድርሻ አካላት ከኢንተርኔት አስተዳደር፤... read more
የ7 ዓመት ህፃን የደፈረው ግለሰብ ከማንኛውም ህዝባዊ መብቶች እንዲታገድ ተወሰነበት
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ የሰባት ዓመት ህፃን ልጅ አስገድዶ የደፈረው በእስራት መቀጣቱን የቃሉ ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል።
ተከሳሹ በእስራት... read more
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የመድሃኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች መመሪያ የግሉን ዘርፍ የሚያበረታታ ነው ተባለ
የመመሪያው መፅደቅ በዘርፉ የሚስተዋለውን ክፍተት ለመሸፈን አስፈላጊ እንደሆነ የገለፁት የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ መመሪያው ግንቦት... read more
በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስቆም በክልሎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA) ያለዕድሜ ጋብቻን፣ የሴት ልጅ ግርዛትን እና ሌሎች ጎጂ... read more
የአውሮፓ መሪዎች ጉባኤን ተከትሎ ዴንማርክ የሁሉም ሲቪል ድሮኖች በረራ ከለከለች
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ዴንማርክ በኮፐንሃገን የሚካሄደውን የአውሮፓ ኅብረት (EU) መሪዎች ጉባኤ ምክንያት በማድረግ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሁሉም... read more
ማዕድ ማጋራት የሰው ተኮር እሳቤያችን ተግባራዊ ማሳያ ነው 👉ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ማዕድ ማጋራት የሰው ተኮር እሳቤያችን ተግባራዊ ማሳያ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው... read more
ምላሽ ይስጡ