መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሚቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያለፈውን የክረምት ወቅት የአየር ጠባይ ግምገማ እና የበጋ ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ይፋ የሚደረግበት መድረክ በዛሬው ዕለት አካሂዷል። ግምገማው የትንበያ ጥራትን፣ ተደራሽነትንና ተጠቃሚነትን ለማሻሻል የሚያግዙ አቅጣጫዎችን ለመለየት እድል የሚፈጥር በመሆኑ፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ሁኔታዎችን ቀድሞ ግንዛቤ እንዲኖር በማድረግ ተገቢ ዝግጅትና የምላሽ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት የገለጹት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እና በዓለም ሚቴዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፈጠነ ተሾመ ናቸው። በመድረኩ የ2018 ክረምት ወራት የዝናብ ስርጭት እና የነበሩ ተጽዕኖዎች፣ እንዲሁም የ2019 የበጋ የአየር ሁኔታ ትንበያ ይፋ ተድርጓል። በአብዛኛው የሀገሪቱ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከመደበኛ በላይ እንደሚሆን የኢንስቲትዩቱ የትንበያ መረጃ ጠቅሷል። ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን ተነስቷል። በአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች በበጋ ወቅት የሚከናወኑ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል። የውሃ አቅርቦትን ከማሻሻል አንጻርም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል። በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ስፍራዎች ላይ የሚጥለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሚሰበሰቡ እና በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችልም ተጠቁሟል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በዛሬው ዕለት በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት እገዛ የሚያደርጉ የክልል፣ የከተማ መስተዳድር እና የፌዴራል ተወካዮች ምርጫ እንደሚከናወን ኮሚሽኑ ገለጸ
ሐምሌ 24 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የስልታዊ ቡድን ምክክር እስከ ትላንት ቀጥሎ እንደዋለም የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው 250... read more
የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እስክታገኝ ድረስ ጥረት ማድረጋችን እንቀጥላለን አሉ
በጉባኤው ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አፍሪካ በዚህ በ21ኛው ከፍለ ዘመን ያነሳችሁ ጥያቄ ተገቢና በቅርቡ... read more
ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ ስለመኖሩ በዝርዝር ገምግሞ በቀጣይ አቋሙን ይፋ እንደሚያደርግ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ገለጸ
ህዳር 01 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በግንቦት ወር ይካሔዳል በተባለው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ፤ ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ ስለመኖሩ በዝርዝር ገምግሞ አቋሙን... read more
በሳውላ ከተማ የ8ኛ ክፍል ፈተና ለተማሪ ሊፈተን የገባ መምህር እና ተማሪው በቁጥጥር ስር ዋሉ
ሰኔ 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሳውላ ከተማ ኩስቲ ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ፈተና ለተማሪ ሊፈተን ከተማሪ ጋር ተመሳስሎ... read more
ኢጋድ የአንካራውን ስምምነት እንደሚደግፍ ገለጸ
ታኅሳስ 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መንግስት መካከል የተደረሰውን ስምምነት እንደሚደግፍ አስታወቀ።
ስምምነቱን... read more
🚨 ሰበር ዜና፦ በአሜሪካ የቢ-52 ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ተከስክሶ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ!
ሰኔ 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ በሚገኘው የኤድዋርድስ የአየር ኃይል እዝ ውስጥ እጅግ አስከፊ የአየር አደጋ ተከስቷል።... read more
የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ በቅርብ ወራት ጸድቆ ሲተገበር ደረጃቸውን ያልጠበቁ የማር ምርቶችን ከገበያ እንደሚያስወጣ ተገለጸ
መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ) በማር ምርት ላይ የሚታየውን የጥራት መጓደል፣ ከሌላ ምርት ጋር ቀላቅሎ ለገበያ የማቅረብ ችግር እና ያለ... read more
አርኪኦሎጂስቶች በፔሩ 3ሺህ 500 ዓመት ዕድሜ ያስቆጠረ ከተማ ማግኘታቸውን ይፋ አደረጉ
ሰኔ 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አርኪኦሎጂስቶች በፔሩ ሰሜናዊ ባራንካ ግዛት ውስጥ ጥንታዊ ከተማ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።
3ሺሕ 500 ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረው ፔኒኮ... read more
የአጥንት ጤና ለጭንቅላት ንቃትና ለትውስታ ያለውን ወሳኝ ሚና ተመራማሪዎች ይፋ አደረጉ
ግንቦት 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) አጥንቶቻችን የሰውነታችንን ቅርፅ ከመያዝ ባለፈ እንደ ልብ እና ሳንባ ሁሉ ንቁ የሆርሞን አመንጪ አካል መሆናቸው... read more
“የሃብት ጉዳይ”የመንግስት ወይስ የህዝብ?
👉
https://youtu.be/cwnRbYU5-xE
read more
ምላሽ ይስጡ