መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ የፕሮጀክቱ ዋነኛ አካል በሆነው የፍልሰት ግንዛቤ ማስጨበጫና የሙያ ስልጠና መሰረት፣ ተመላሾችን በተለያዩ የሙያ መስኮች አሰልጥኖ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው እለት ማስመረቁን አስታውቋል። በ10ኛው ዙር የስልጠና መርሃ ግብሩ ለ30 ወጣቶች ስልጠና ሰጥቶ ማስመረቅ መቻሉን የንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል መለሰ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። ከስደት ተመላሽ ወጣቶቹ በምግብ ዝግጅት፣ በውበት ሳሎን፣ በቤት አያያዝና ላውንደሪ፣ እንዲሁም በልጆች እንክብካቤ የሙያ መስኮች ላይ ስልጠና መውሰዳቸውንም ገልጸዋል። ተቋሙ ከተቋቋመ ገና ሁለተኛ ዓመቱ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፤ ወጣቶች በሀገራቸው የሥራ እድል ፈጥረው እንዲሰሩና በፍልሰት ዙሪያ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ የሚያግዙ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ አብራርተዋል። በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ 30 ወጣቶችን አሰልጥኖ ቢያስመርቅም፣ ወደፊት ቁጥራቸው በርከት ያሉ ሰልጣኞችን በተለያየ የሙያ ስብጥር አስመርቆ ሥራ ለማስቀጠር እንደሚሰራ ተገልጿል። አሁን ላይ ከተመረቁት 30 ከስደት ተመላሽ ወጣቶች መካከል 11ዱ ሥራ መጀመራቸውን አቶ ዳንኤል ተናግረዋል። ቀሪዎቹ ሰልጣኞችም በቅርቡ ሥራ እንደሚያገኙ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ስምሪት አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሰብሃዲን ሱልጣን አስታውቀዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ሚዲያዎች በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን የመረጃ ፍሰት በሰላማዊ መንገድ በማስተዳደር ለህዝቡና ለሃገሪቱ የሚበጁ ዘገባዎችን በሃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በፖለቲካዊ ሁኔታዋ ላይ እያለፈች ባለችው ወሳኝ ጊዜ ሚዲያዎች በሃላፊነት እና በተጠያቂነት መረጃ ማቅረብ እንዳለባቸው ምሁራን ለመናኸሪያ ሬዲዮ... read more
ለነዳጅ ኩባንያዎች እና ማደያዎች ወደ ህጋዊ ስርዓት እንዲገቡ ማሳሰቢያ ተሰጣቸዉ
በህገ-ወጥነት ተግባር ላይ የተሰማሩ የነዳጅ ኩባንያዎች እና ማደያዎች ወደ ህጋዊነት እንዲገቡ ማሳሰቢያ መሰጠቱን የገለጹት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሳሁን... read more
የትምህርት ሚኒስትር የዩኒቨርሲቲዎች በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ የሚመደብ ይሆናል ቢልም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በበጀት ጉዳይ እንደማይመለከተው እና ስምምነቱ ተግባራዊ ቢደረግ በትምህርት ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚፈጥር ተገለጸ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ የዩኒቨርሲቲዎች በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ የሚመደብ ይሆናል... read more
ኢትዮጵያን ወደ AUSSOM ለመመለስ ውይይቶች እየተካሄዱ ነው ተባለ
ታኅሳስ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያና ሶማሊያ አልሻባብን በጋራ ለመዋጋት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ኢትዮጵያና ሶማሊያ ባለፉት ጥቂት... read more
የብሪክስ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ከአዳዲስ የገንዘብ ምንጮች ተጠቃሚ እንድትሆን እና በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሳትፎ ለማሳደግ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ተገለጸ
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል አገራት ልማት ባንክ (New Development Bank) አባል ለመሆን በይፋ ጥያቄ ማቅረቧ ተገልጿል። ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ ኢትዮጵያ ለተለያዩ... read more
በአፋር ክልል ፈንታሌ አካባቢ ተገኘ ስለተባለው የሚቴን ጋዝ ጥናት የሚያደርግ የባለሙያ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩ ተገለጸ
ኢሮፕያን ሳተላይት ባወጣው መረጃ በፈንታሌ ወረዳ ከወራት በፊት ሲከሰት የነበረውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ ባልተለመደ መልኩ ሚቴን የተሰኘ የተፈጥሮ ጋዝ መገኘቱን... read more
ፊሊፒንስን የመታው ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ የሟቾች ቁጥር 69 ደረሰ
መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ፊሊፒንስን የመታውን ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ፣ የሟቾች ቁጥር ወደ 69 ከፍ ማለቱን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ። የነፍስ... read more
መራጮችና ዕጩዎች በኦንላይን መመዝገብ የሚችሉበት ሶፍትዌር ተዘጋጀ
ሰኔ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ መራጮችና ዕጩዎች ካሉበት ሆነው በኦንላይን መመዝገብ የሚችሉበት... read more
ጡረታ የወጡ አረጋውያን ተደራጅተው በሙያቸው አመቺ በሆነ የስራ መስክ እንዲሰማሩ ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ
ኅዳር 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) እድሜያቸው ከ60 አመት በላይ የሆኑና ጡረታ የወጡ ነገር ግን የመስራት አቅም ያላቸው አረጋውያን በሙያቸው ተሰማርተው... read more
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቁጥርን መጨመር የቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ሽግግርን ያፋጥናል ተባለ
የኤሌክትሪክና ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች አገር አቀፍ ረቂቅ ስትራቴጂ ላይ ዘርፉ ከሚመለከታቸው ሚኒስቴር መ/ቤቶች፤ ሚኒስትሮችና የተቋማት አመራሮች ጋር የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ... read more
ምላሽ ይስጡ