መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ የፕሮጀክቱ ዋነኛ አካል በሆነው የፍልሰት ግንዛቤ ማስጨበጫና የሙያ ስልጠና መሰረት፣ ተመላሾችን በተለያዩ የሙያ መስኮች አሰልጥኖ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው እለት ማስመረቁን አስታውቋል። በ10ኛው ዙር የስልጠና መርሃ ግብሩ ለ30 ወጣቶች ስልጠና ሰጥቶ ማስመረቅ መቻሉን የንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል መለሰ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። ከስደት ተመላሽ ወጣቶቹ በምግብ ዝግጅት፣ በውበት ሳሎን፣ በቤት አያያዝና ላውንደሪ፣ እንዲሁም በልጆች እንክብካቤ የሙያ መስኮች ላይ ስልጠና መውሰዳቸውንም ገልጸዋል። ተቋሙ ከተቋቋመ ገና ሁለተኛ ዓመቱ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፤ ወጣቶች በሀገራቸው የሥራ እድል ፈጥረው እንዲሰሩና በፍልሰት ዙሪያ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ የሚያግዙ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ አብራርተዋል። በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ 30 ወጣቶችን አሰልጥኖ ቢያስመርቅም፣ ወደፊት ቁጥራቸው በርከት ያሉ ሰልጣኞችን በተለያየ የሙያ ስብጥር አስመርቆ ሥራ ለማስቀጠር እንደሚሰራ ተገልጿል። አሁን ላይ ከተመረቁት 30 ከስደት ተመላሽ ወጣቶች መካከል 11ዱ ሥራ መጀመራቸውን አቶ ዳንኤል ተናግረዋል። ቀሪዎቹ ሰልጣኞችም በቅርቡ ሥራ እንደሚያገኙ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ስምሪት አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሰብሃዲን ሱልጣን አስታውቀዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ብርቱካን ተመስገንን ጨምሮ በሽብር ወንጀል ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ
ፍርድ ቤቱ ብርቱካን ተመስገንን ጨምሮ በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ የ14 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል፡፡
ፖሊስ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት... read more
🔰ከጨለማ የተገኘ ብርሃን
👉የኳንተም ፊዚክስ አስገራሚ ግኝት
ሰኔ 23 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሳይንስ ሊቃውንት ሙሉ በሙሉ ከሚመስል ጨለማ ውስጥ ብርሃን እንዴት እንደሚመጣ ማስመሰል... read more
የደቡብ አፍሪካ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በእንግሊዝ መንግስት ቪዛ መከልከላቸውን ተቃወሙ
የኢኮኖሚ ፍሪደም ፋየርስ ፓርቲ መሪ ጁሊየስ ማሌማ በእንግሊዝ ሊያደርጉት የነበረው ጉብኝት በቪዛ ምክንያት ከጉዞ መታገዳቸውን መርህ አልባ ሲሉ ተችተውታል።
የምዕራባውያን ኢምፔሪያሊዝም... read more
የቡና ከረጢቶችን የፈጠራ አቅም ከባንግላዲሽ መማር እንደሚያስፈልግ ተነገረ
ሕዳር 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቡና ከረጢቶችን የፈጠራ አቅም ከባንግላዲሽ መማር እንደሚያስፈልግ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ይድነቃቸው ወርቁ... read more
ጊዜዉ ያለፈበት መድሃኒት ቀላቅለዉ ሲሸጡ በተገኙ 105 የመድሃኒት መሸጪያ መደብሮች ላይ አስተዳደረዊ እርምጃ ተወሰደ
በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ መድኃኒት መደብሮች የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ቀላቅለው ይዘው የተገኙና አላግባብ ያስቀመጡ 105 ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ... read more
በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ሩዝን በስፋት ለማምረት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ሩዝን በስፋት ለማምረት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ በሪሶ ፈይሳ፤በ2017/18 መኸር እርሻ... read more
ትርክትና ታሪክ ወለድ ችግሮችን ለመፍታት ምሁራን ሃሳብ እንዲያዋጡ ተጠየቀ
በቀሪ የሀገራዊ ምክክር ሂደት የምሁራን ሚና ከፍ ማለት እንዳለበት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ ባካሄደው ውይይት አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ዛሬ ሰኔ 9... read more
”ኢትዮጵያ ላይ ማንም ሀገር ወረራ ሊፈጽም አይችልም፤ማንም ደፍሮ አይሞክረንም” – ዐቢይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ ለምክር ቤቱ የሰጡት ማብራሪያ 👉
https://youtu.be/rxU3cUbE1RQ
read more
ማኅበራዊ ሚዲያ ተከፍቶላቸው እንዲወያዩ የተደረጉት ሮቦቶች ውይይታቸው በጦርነት ተጠናቀቀ
ነሐሴ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአምስተርዳም ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በቅርቡ ባደረጉት አስገራሚ ጥናት፣ 500 ቻትቦቶችን (AI ሮቦቶችን) ያሳተፈ የማኅበራዊ ሚዲያ ሙከራ... read more
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞው ዋና ስራ አስፈጻሚ ካፒቴን መሐመድ አሕመድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ኅዳር 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ን እ.ኤ.አ ከ1980 እስከ 1991 ዓ.ም በዋና ስራ አስፈፃሚነት በማገልገል ለአየር መንገዱ... read more
ምላሽ ይስጡ