ነሐሴ 28 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮ ቴሌኮም “NEXT Horizon – Year 2” በሚል የ2018/19 በጀት ዓመት ዕቅዱን ይፋ አድርጓል። በዚህም መሠረት ቴሌ ከቁጥር ባሻገር በሚል መርሕ አካታችና ዘመናዊ የሆኑ፣ ሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን ለመሥራት ማቀዱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱ 6 የትኩረት አቅጣጫዎችን ይዞ እንደሚሠራ አመላክተው፣ 7 ከተሞችን የ5G ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን ገልጸዋል። በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ 1 ሺህ 625 አዳዲስ የሞባይል ኔትወርኮችን ለመገንባት እንደታቀደና፣ በዓመቱ መጨረሻም በመላ አገሪቱ ከ12 ሺህ በላይ የሞባይል ኔትወርኮች እንደሚኖሩ ተናግረዋል። ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 300 አዳዲስ ከተሞችን የ4G ተጠቃሚ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን፣ ሁለተኛው የሆራይዘን ዓመት ሲጠናቀቅ በአጠቃላይ 70 ከተሞች የ5G ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገልጻል። እንዲሁም 150 ሺህ ደንበኞችን ከኮፐር መስመር ወደ ፋይበር ለማዘዋወርና ከ6 ሺህ በላይ የሰርቨር ዝርጋታ ለማከናወን ታቅዷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ