ነሐሴ 30 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ ሥር ከሚገኙ ድርጅቶች አንዱ የሆነው ጎዶ ሀውሲንግ ኤንድ ስማርት ሪልስቴት የሚያስገነባቸውን ቤቶች ለገዢዎች የሚያስተዋውቅበትን ኤግዚቢሽን በዛሬው ዕለት ከፍቷል፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ መሥራች እና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደረጄ ማሙዬ፣ ለትውልድ መተላለፍ የሚችል ቤትን በጥራትና በቴክኖሎጂ አስደግፎ መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ድርጅቱ በአዲስ አበባ ከተማ በ10 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈና 27 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚደረግበት ሪል እስቴት እየገነባ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡ እስካሁን 500 ቤቶች መሸጣቸውን የተናገሩት አቶ ደረጄ፣ ቀሪዎቹን 200 ቤቶች ለመሸጥ ኤግዚቢሽኑ መከፈቱን አክለዋል፡፡ ተቋሙ በአሥር ዓመት ውስጥ አምስት መቶ ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ዕቅድ ይዞ ወደ ሥራ መግባቱን የገለጹት አቶ ደረጄ፣ በቀጣይም የቤቶቹ ልማት ከአዲስ አበባ ከተማ ባሻገር ወደ ተለያዩ ከተሞች የሚስፋፋ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ሪል እስቴቱን ለማጠናቀቅ የ30 ወራት ዕቅድ መያዙን በመግለጽ፣ የሀገሪቱን የቤት እጥረት ለመፍታት እንደሚሠሩም ጠቁመዋል፤ ኤግዚቢሽኑም እስከ ጳጉሜ 3 ድረስ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ከተካሄደ በኋላ እስከ መስከረም 30 ድረስ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ አመልክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ