መስከረም 1 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የየመን ሁቲ አማፂያን በቀይ ባሕርና በኤደን ባህረ ሰላጤ መካከል በሚገኘውና ለዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ወሳኝ በሆነው የባብ ኤል-ማንደብ ወደብ አፍ ላይ የምትገኘውን ስትራቴጂካዊዋን ፔሪም (ማዩን) ደሴት መቆጣጠራቸውን የየመን መንግስት ምንጮች አስታወቁ። በሳውዲ አረቢያ የሚደገፉት የየመን ህጋዊ መንግስት ሀይሎች ከደሴቷ እና በቅርብ ከሚገኘው የዱባብ የባህር ዳርቻ ከተማ ማፈገፈጋቸውን ተከተሎ ሁቲዎች ቦታውን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩት በፈጣን የማጥቃት እርምጃ ነው። አማፂያኑ ከዚህ ቀደም ታሪካዊቷን የመንደብ ወደብ ከተማ ሞካን መቆጣጠራቸው ይታወሳል። ይህ የሁቲዎች እንቅስቃሴ በዓለም አቀፉ የኃይልና የንግድ መርከቦች ዝውውር ላይ ከፍተኛ ስጋት የደቀቀ ሲሆን፣ ቡድኑ በዓለም ላይ ካሉት ዋና ዋና የባህር መስመሮች አንዱ የሆነውን የባብ ኤል-ማንደብ መተላለፊያን በቁጥጥሩ ስር ለማዋል ያስችለዋል ተብሏል። የየመን መንግስት ወታደራዊ አካላት በበኩላቸው በአካባቢው የአየርና የመሬት ጥቃት በመሰንዘር በሁቲዎች የተያዙትን ስትራቴጂካዊ ቦታዎች መልሰው ለመቆጣጠር የመልሶ ማጥቃት እርምጃ እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።
___
ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
ምላሽ ይስጡ