ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን በደቡብ ኮሪያዋ የጄጁ ደሴት አቅራቢያ የሚካሄደውን “ፍሪደም ኤጅ” (Freedom Edge) የተሰኘውን የጋራ የጦር ልምምድ እንደሚያካሂዱ ተገልጿል። ይህ ስምምነት ይፋ የሆነው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሴኦል ጋር ይደረጉ የነበሩ የጋራ የጦር ልምምዶችን ለመቀነስና የባህር ኃይል ኮርፕስ (Marine Corps) ልምምዶችን ለመሰረዝ ከወሰኑ በኋላ በመሆኑ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። የደቡብ ኮሪያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም እንዳስታወቁት፣ ይህ የሶስትዮሽ ልምምድ በዋናነት በሚሳይል መከላከያ፣ በባህር ሰርጓጅ መርከቦች ውጊያና በባህር ላይ ደህንነት ዙሪያ የሀገራቱን ቅንጅት ለማጠናከር ያለመ ነው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወጪን ለመቀነስና ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያለውን የዲፕሎማሲ በር ለመክፈት በሚል ባለሁለት ወገን የጦር ልምምዶችን ቢቀንሱም፣ የሶስቱ ሀገራት የጋራ ዝግጁነት ግን በእቅዱ መሰረት እንደሚቀጥል ተመልክቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ