ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓለማችን እጅግ አደገኛ እና ተለዋዋጭ በሆነው የፓሲፊክ ውቅያኖስ «የእሳት ቀለበት» (Ring of Fire) ቀጠና ውስጥ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ187 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች መመዝገባቸው ተገለጸ። ከደቡብ አሜሪካ ምዕራባዊ ጠርዝ ተነስቶ በማዕከላዊና ሰሜን አሜሪካ፣ አላስካ፣ ጃፓን፣ ፊሊፒንስ፣ ኢንዶኔዥያ እና ኒውዚላንድን አቋርጦ 40 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ይህ ግዙፍ ቀጠና፣ በርካታ የመሬት ሰሌዳዎች እርስ በእርስ የሚጋጩበት በመሆኑ ለእንቅስቃሴው ዋና ምክንያት ሆኗል። የመሬት ውስጥ ጫናዎች በየጊዜው በሚፈጥሩት ስብራት ሳቢያ በየቀኑ የመሬት መንቀጥቀጥና እሳተ ገሞራ ፍንዳታዎች የሚከሰቱበት ይህ ቀጠና፣ ምንም እንኳ የ7 ቀናቱ የ187 መንቀጥቀጦች ቁጥር ከፍተኛ ቢመስልም፣ ከቀጠናው የተፈጥሮ ባህሪ አንጻር ድንገተኛ ግዙፍ አደጋ ወይም የከፋ እሳተ ገሞራ መከሰቱን የሚያሳይ እርግጠኛ ምልክት ላይሆን እንደሚችል ባለሙያዎች አስታውቀዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ