ነሐሴ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)
በአሜሪካ በሚገኙ ሰባት ክፍለ ሀገራት ውስጥ የሚሰሩ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የቴክኖሎጂ የመረጃ ማዕከላት (Data Centers) የሚጠቀሙት የውሃ መጠን ከመላው የካሊፎርኒያ ግዛት ከተሞች አጠቃላይ የቤት ውስጥ የውሃ ፍጆታ መብለጡን አዳዲስ የምርምር ዘገባዎች አመላክተዋል።
እነዚህ በቨርጂኒያ፣ ቴክሳስ፣ ካሊፎርኒያ፣ ኦሪገን፣ አሪዞና፣ ኢሊኖይ እና ጆርጂያ የሚገኙ ግዙፍ የመረጃ ማዕከላት በውስጣቸው ያሉትን ሃይል አውጪ ሰርቨሮች ለማቀዝቀዝ እና ኤሌክትሪክ ለማመንጨት በየቀኑ በቢሊዮን የሚቆጠር ጋሎን ንጹህ ውሃ ይጠቀማሉ።
የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ ሞዴሎችን ለማሰልጠን እና ለማስኬድ የሚያደርጉት ውድድር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ፣ የውሃ ፍጆታቸውም በተመሳሳይ ፍጥነት እያደገ መጥቷል።
የአካባቢ ጥበቃ ተመራማሪዎች እና የሃብት ባለሙያዎች ይህ ሁኔታ በአካባቢው በሚገኙ የመጠጥ ውሃ እና የመሬት ውስጥ ውሃ ሀብቶች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም በድርቅ በሚመቱ ቀጣናዎች የሚገኙ የመረጃ ማዕከላት አሰራራቸውን ይበልጥ ግልጽ እንዲያደርጉ እና ውሃን መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውሉ ዘመናዊ የማቀዝቀዣ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙ ጥሪዎች እየቀረቡ ይገኛሉ።
_
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ