
ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)ድርጅቱ አዲሱን ምዕራፍ ምክንያት በማድረግ፣ ለመኖሪያና ለንግድ ቤት ገዢዎች እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ልዩ የበዓል ቅናሽ ማቅረቡንም ይፋ አድርጓል። ድርጅቱ ባቀረበው መረጃ መሠረት፣ ከ55 ካሬ ሜትር ስቱዲዮ ጀምሮ እስከ ባለ 3 መኝታ 165 ካሬ ሜትር የመኖሪያ አፓርትመንቶች እና የንግድ ሱቆች በሽያጭ ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።
የመኖሪያና የንግድ ቦታዎቹ ዋጋ በካሬ ሜትር ከብር 80 ሺህ 500 ጀምሮ የተመደበ ሲሆን፣ እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ልዩ የዋጋ ቅናሽ የቀረበበት ይህ ዕድል እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ብቻ የሚቆይ ነው ተብሏል። እንዲሁም ከነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአትላስ ሳይት ላይ የሽያጭ ዘመቻ መጀመሩንም ድርጅቱ አስታውቋል።
በተጨማሪም ደንበኞች በተዋዋሉበት የኢትዮጵያ ብር መጠን ብቻ ክፍያቸውን አጠናቀው በወቅቱ የሚረከቡበት የዋጋ ዋስትና መመቻቸቱም ተገልጿል።
ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የማኅበረሰብ ተሳትፎ ኃላፊነቱን ለመወጣት በአንድ የበጎ አድራጎት ተቋም እና ለሁለት ትምህርት ቤቶች ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቋል።
ባለፉት አሥር ዓመታት ያሥሚን ጀማል ኮንስትራክሽን በሚል ስያሜ የሪል ስቴት ፕሮጀክቶችን በመገንባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያበረክት መቆየቱን የገለጸው ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ፣ አሁን ላይ ልምድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያን እና ቻይናውያን ባለሙያዎችን በማጣመር በኢንዱስትሪው ውስጥ አዲስ የጥራትና የፍጥነት መለኪያ ለማስቀመጥ እየሠራ እንደሚገኝም ገልጿል።
ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ ከዚህ ቀደም በውጤታማነት ካጠናቀቃቸው እና በመገንባት ላይ ካሏቸው ፕሮጀክቶች መካከል ባለ 5 እና 12 ወለል 14 የመኖሪያ አፓርትመንት ብሎኮች ይገኙበታል ተብሏል።
በአሁኑ ሰዓት ደግሞ አዳዲስ የገበያ አማራጮችን ለማስፋት በመስቀል ፍላወር፣ በቄራ፣ በካዛንቺስ እንዲሁም በአትላስ ባለ 15 ወለል ዘመናዊ ሕንፃዎች ግንባታ መጀመሩን ተቋሙ አስታውቋል። ድርጅቱ የቤት አቅርቦት እጥረትን ለመቅረፍ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር እንደሚሠራም አስታውቋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ