ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በዓለም አቀፉ የሰው ሰራሽ አስተውሎትና የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት አስደናቂ ክስተት ተመዝግቧል።
ቲያንጎንግ አልትራ (Tiangong Ultra) በመባል የሚታወቀውና በቻይና የቴክኖሎጂ ተመራማሪዎች የበለጸገው ሂውማኖይድ ሮቦት፣ 100 ሜትር ርቀትን በ8.64 ሰከንድ ብቻ በማጠናቀቅ አዲስ የዓለም የፍጥነት ሪከርድ ባለቤት መሆን ችሏል።
ይህ ስኬት የሮቦቶች የእንቅስቃሴ ቅልጥፍና፣ ሚዛን የመጠበቅ ብቃት እና የኃይል አጠቃቀም ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያሳይ አብዮታዊ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል። ሮቦቱ በከፍተኛ ፍጥነት በሚሮጥበት ወቅት ሰውነቱንና እግሮቹን ከስበት ጋር አጣጥሞ ለማስኬድ የተቀረጸው የላቀ የቁጥጥር ስልተ-ቀመር (control algorithm) እና የሞተር ቴክኖሎጂ ለውጤቱ መገኘት ዋና ምክንያት መሆናቸውን የዘርፉ ባለሙያዎች ገልጸዋል።
የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት፣ ሂውማኖይድ ሮቦቶች ከዚህ ቀደም በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ላይ የነበረባቸውን የዝግተኝነትና የክብደት እንቅፋት በጥ በጥ እየተሻገሩ መምጣታቸውን ይህ አዲስ ሪከርድ ማረጋገጫ ነው።
ሮቦቱ ያስመዘገበው አስደናቂ የፍጥነት ውጤት በቴክኖሎጂው ዓለም ከፍተኛ አድናቆትን ያገኘ ሲሆን፣ ወደፊት በኢንዱስትሪ፣ በቁስ ማጓጓዝ፣ በአደጋ ጊዜ ፍለጋና አድኖ የማዳን ስራዎች እንዲሁም በሰው ሰራሽ ረዳትነት ዘርፍ የሚኖረውን ሚና የበለጠ ያጎለብተዋል ተብሎ ይጠበቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ