ነሐሴ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት የሚያጋጥሙ የሠላም መደፍረሶችን ለመፍታት የተለያየ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር ገልጾ፣ አሁንም ቢሆን ለግጭት ራስን ማነሳሳቱ ዋጋ ስለሚያስከፍል አለመግባባቶችን በንግግር መፍታት ያስፈልጋል ብሏል።
የጉባኤው ምክትል ጠቅላይ ጸሐፊ አቶ መስዑድ አደም በባለፈው የሰሜኑ ጦርነት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጦርነቱን ማስቀረት ባይቻለው እንኳ ሁሉም ከጦር መሣሪያ ይልቅ ንግግርን እንዲያስቀድሙና ልዩነቶቻቸውን በፖለቲካ ድርድር እንዲፈቱ ለማድረግ የራሱን ጥረት ማድረጉን አስታውሰዋል።
አሁንም ቢሆን ጉባኤው ጦርነት መፍትሔ ሊሆን እንደማይችል በመግለጽ ሁሉም ሠላምን እንዲያስቀድሙ ጠይቀዋል። ይሁን እንጂ «ጉባኤው ልክ እንደ ባለፉት ጊዜያት ግጭቶች እንዳይከሰቱ ምን ዓይነት ጥረት እያደረገ ይገኛል?» ለተባለው ጥያቄ፣ አሁን ላይ ይህ ነው የሚባል ጥረት እያደረገ እንደማይገኝ በመግለጽ በቀጣይ ውይይት በማድረግ ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሁንም ወደ ግጭት ከመገባቱ በፊት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሠላምን እንዲያስቀድሙ ጥሪ አቅርቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ