ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢሎን መስክ ኩባንያ የሆነው ስፔስኤክስ (SpaceX) እንደ ይፋዊ ኩባንያ የመጀመሪያውን የሩብ ዓመት የገቢ ሪፖርት ካቀረበ ማግስት የአክሲዮን ዋጋው ከ13 በመቶ በላይ ቅናሽ አሳየ።
የኩባንያው የካፒታል ወጪ እጅግ ማደጉ ባለሀብቶችን ስጋት ላይ የጣለ ሲሆን፣ ወጪው 18.37 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የስድስት እጥፍ ጭማሪ ያሳየና ተንታኞች ከጠበቁት 13.2 ቢሊዮን ዶላር በጣም የላቀ ሆኖ ተመዝግቧል።
ከዚህ ግዙፍ ኢንቨስትመንት ውስጥ አብዛኛው ማለትም 15.8 ቢሊዮን ዶላሩ የተመደበው ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) መሠረተ ልማት ግንባታ ነው። ይህም የ AI ሞዴሎችን በትልቅ ደረጃ ለመገንባት፣ ለማሰልጠን፣ ለማሰማራት እና ለማስኬድ የሚያስፈልጉ ልዩ የኮምፒዩቲንግ፣ የማከማቻ፣ የኔትወርክ እና የሶፍትዌር ሥርዓቶችን ያካትታል።
በተጨማሪም ስፔስኤክስ የዳታ ሴንተሮቹን የማስተናገድ አቅም አሁን ካለበት 1.4 ጊጋዋት እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ወደ 2 ጊጋዋት ማሳደግ እንደሚፈልግ አስታውቋል።
በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች በእነዚህ ትላልቅ የ AI መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንቶች ላይ የሚወጡት ግዙፍ ወጪዎች በእርግጥ ተመላሽ አላቸው ወይ የሚለውን ጥያቄ በስፋት እያነሱ ይገኛሉ። የኢቶሮ (eToro) ዋና ተንታኝ ጆሽ ግልበርት እንደገለጹት፣ ባለሀብቶች ያለገደብ የሚወጡ ወጪዎችን በመቃወም የሚጨበጥ ትርፍ መጠየቅ በጀመሩበት በዚህ የውጤት መግለጫ ወቅት፣ መሰል ጥብቅ ግምገማዎች በታላላቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ሲያርፉ ቆይተዋል። ስፔስኤክስ ባለአክሲዮኖቹ በምህዋር (ኮንደላ) ውስጥ የሚገነቡ ዳታ ሴንተሮችን እንዲደግፉ በመጠየቁ፣ ይህንን ፈተና በተላቀቀ ደረጃ እንደሚጋፈጠው ተመልክቷል።
በሌላ በኩል ስፔስኤክስ የኮምፒዩቲንግ አቅሙን ለግሮክ (Grok) ሞዴሎቹ አገልግሎት ከማዋሉም በላይ ለሌሎች በንቃት እንደሚሸጥ ገልጾ፣ 14.1 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የክላውድ አገልግሎት ስምምነቶችን መያዙን ይፋ አድርጓል።
ኩባንያው የተወሰነ ትርፍ ያየበት ብቸኛ መስክ የኮሙኒኬሽን ንግዱ ሲሆን፣ የስታርሊንክ (Starlink) የሳተላይት ግንኙነት አገልግሎት ተመዝጋቢዎች ቁጥር በሁለት እጥፍ በመጨመር 12 ሚሊዮን ደርሷል። በመሆኑም ገቢው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ66 በመቶ እድገት በማሳየት 1.66 ቢሊዮን ዶላር የሥራ ማስኬጃ ገቢ ማስገኘት ችሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የጎዳና ተዳዳሪዎችን ሙሉ መረጃ የማስመዝገብ ግዴታ ለሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደተሰጠው ተገለጸ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን በትላንትናው እለት ባካሄደበት ወቅት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎዳና... read more
አራት የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች መመዘኛዎቹን በማሟላት አሸናፊ ሆኑ
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለግል ኩባንያዎች ነዳጅ እንዲያቀርቡ መፈቀዱን ተከትሎ ባካሄደው ዓለም አቀፍ ጨረታ 4 ኩባንያዎች አሸናፊ መሆናቸውን ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ነዳጅ... read more
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በ2017 ዓ.ም ከቅጣት 404 ሚሊዮን ብር ገቢ ማሰባሰቡን አስታወቀ
ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከድርጅቶች፣ ከግለሰቦች እና ከመንግስት ተቋማት የተጣለባቸውን የቅጣት... read more
አሁንም ድረስ በተለያዩ መንገዶች በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ ሀገራት መኖራቸው ተገለጸ
ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ሉዓላዊነቷን የሚገዳደሩ የውጭ ሀይሎች ሲገጥሟት እንደነበር ይታወቃል፡፡
ይህ አይነቱን ጣልቃ ገብነት ለማስወገድ የሀገር ሀብትን በአግባቡ መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን... read more
ጃን ሜዳ እና አቃቂ ቃሊቲ ታቦት ማደሪያ በሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ሆነዋል
ጥር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከጥር 10 እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ጃን ሜዳ እና አቃቂ ቃሊቲ ታቦት... read more
የቴኳንዶ ስፖርት በበጀት ችግር ምክንያት የታሰበውን ያህል እያደገ አለመሆኑ ተገለጸ
እንደ ሀገር ህብረተሰቡ እንዲሁም ስፖርቱን ከመንግስት በተጨማሪ ይደግፋሉ ተብለዉ የሚታሰቡ ባለሀብቶች ስለ ቴኳንዶ ስፖርት ግንዛቤው ስለሌላቸው ተደጋጋሚ የበጀት እጥረት እንዲገጥመው... read more
የንስር ዓይን አስገራሚ ሚስጥር
👉ከ10ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ መሬት ላይ ያለውን ጉንዳን መመልከት ይቻላል ተብሏል
ነሐሴ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ንስር በአለም ላይ ካሉት ፍጥረታት... read more
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ታላቅ ፍፃሜ፤ አርሰናል ከፓሪስ ሴንት ጄርሜን
ግንቦት 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በየዓመቱ ከሚከናወኑ እና የክለቦች ፉክክር ከሚደምቅበት እንዲሁም በአውሮፓ ውስጥ ሀያሉ ክለብ ለመባል የሚደረግ የክለቦች ትንቅንቅ... read more
በከተማዋ ላይ የታይሮይድ መድሃኒት ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመሆኑ አሳስቦናል ሲሉ ተጠቃሚዎች ገለጹ
ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለመናኸሪያ ሬዲዮ ቅሬታቸውን ያቀረቡት የእንቅርት መድሃኒት (ታይሮክሲን) ተጠቃሚ መድሃኒቱን የመንግስት መድሃኒት መሸጫ በሆነው ከነማ መደብር... read more
ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት ሆነው ተመደቡ
ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማሕቀፍ ኮንቬንሽን መሠረት የኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሀገር መሆኗን ተከትሎ... read more
ምላሽ ይስጡ