ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)አገልግሎቱ 100 የከባድ ጭነት ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆኑንም ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ሀገሪቱ የደረሰችበትን የዕድገት ደረጃ የሚመጥን የከባድ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት ለመዘርጋት የ5 ዓመት ዕቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነም ይታወቃል፡፡
የአገልግሎቱ የማርኬቲንግ መምሪያ ኃላፊና ተወካይ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደምሰው በንቲ፤ በመርከብ፣ በከባድ ተሽከርካሪዎችና በሌሎችም ዘርፎች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ታቅዶ በዚህ ዓመት ብቻ 100 የከባድ ተሽከርካሪዎችን በመግዛት አጠቃላይ ቁጥሩን ወደ 6 መቶ 52 ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ የወደብ ፍላጎቷን ለማሟላት በርካታ ሥራዎችን እየሠራች ባለችበት በአሁኑ ወቅት፤ ፈጣን፣ ዘመናዊና በተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮች የተሳሰሩ አሰራሮችን መዘርጋት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ አሁን ላይ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚያስችል መልኩ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ለማስገባት በሂደት ላይ መሆናቸውን አቶ ደምሰው ተናግረዋል፡፡
የባህር ትራንስፖርት ዘርፉ በሰው ሀብት ማብቃት፣ በዘመናዊ አሠራርና በመሣሪያ አቅርቦት ረገድ በሚጠበቀው ልክ አይደለም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ እነዚህን ክፍተቶች ለማሟላት የ5 ዓመት ዕቅድ ተነድፎ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠትና አሠራሩን ለማቀላጠፍ በርካታ የማሻሻያ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ዲዲዬ ዴሾ የሪያል ማድሪድ ቀጣይ አሰልጣኝ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቆመ
ሚያዚያ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ዲዲየር ዴሻምፕ ከ2026 የዓለም ዋንጫ በኋላ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንን እንደሚለቁ ማረጋገጣቸውን ተከትሎ፣ የሪያል ማድሪድ ቀጣይ አሰልጣኝ... read more
ሕልሞቻችንን እንደ ፊልም መመልከት
👉አዲስ የሕልም መቅጃ ቴክኖሎጂ ይፋ ተደረገ
ሰኔ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ሳይንቲስቶች ሕልሞቻችንን መቅዳትና መልሶ ማጫወት የሚችል አብዮታዊ አዲስ ሄድሴት ይፋ አደረጉ።... read more
በአሜሪካ ላሞች ላይ የVR መነጽር በማድረግ ጭንቀታቸው እንዲቀንስ እየተደረገ ነው ተባለ
👉መነጸሩ አረንጓዴ ሜዳዎችን እንዲያዩና ብዙ ወተት እንዲያመርቱ ያግዛቸዋል ነው የተባለው
ነሐሴ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ በሚገኙ አንዳንድ እርሻዎች ላሞች በረት... read more
እንደ ሀገር ይህ ነው ተብሎ የተለየ ስያሜ የሚሰጠው የኢኮኖሚ ርዕዮት ዓለም እንደሌለ ተገለጸ
ኅዳር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሁን ላይ እንደ ሀገር የምንከለተው የኢኮኖሚ ስርዓት አፈጻጸሙና መልኩ ካፒታሊስት ይምሰል እንጂ ቅይጥ ኢኮኖሚ፣ ካፒታሊስት... read more
ምርጫ ቦርድ በተለያዩ አካባቢዎች ለእስር የተዳረጉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራርና አባላት እንዲፈቱ እየወተወትኩ ነዉ አለ
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎችና አመራሮች ላይ የሚደረገውን አስርና መንገላታትን እንደሚያቅና ይህንኑ ችግር ለመፍታት ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
የብሄራዊ ምርጫ... read more
አንድ መርማሪ በግዴታ ስራ ላይ እያለ ከአቅሙ በላይ በሆነ መንገድ ከግድያ ውጪ ማንኛውንም ወንጀል ከፈፀመ ተጠያቂ የማይሆንበት አንቀጽ በምክር ቤት ጸደቀ
👉ይህ አይነቱ አንቀጽ ዜጎችን ለሰብዓዊ መብት ጥስት የሚያጋልጥ ነው ሲሉ የምክር ቤት አባላት ተቃዉሟቸዉን ገልጸዋል፡፡
ሰኔ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሕዝብ... read more
42ኛው የሻምበል አበበ በቂላ ማራቶን የፊታችን እሁድ በሀዋሳ ከተማ በድምቀት ይካሄዳል
ሰኔ 18 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) 42ኛው የሻምበል አበበ በቂላ ማራቶን የፊታችን እሁድ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና ሀዋሳ ከተማ በድምቀት... read more
የዓለም ረጅሙን የሥራ ዘመን ያስመዘገቡት የ100 ዓመቱ አዛውንት ክብረ ወሰን ሰበሩ
ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዋልተር ኦርትማን የተባሉ ብራዚላዊ አዛውንት በአንድ ኩባንያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በመሥራት የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት... read more
የብሔር ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ እንደ ካላንደር መታየት የለበትም ተባለ
https://youtu.be/k43lj7ZNPrw
read more
የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የኢ- ሰርቪስ አገልግሎት ማስጀመሩን አስታወቀ
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥራት ያለው፣ ቀልጣፋና ምቹ የሆነ አገልግሎትን ለመስጠትና እንደ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በቂ የህግ ጥበቃ ለማድረግ የኢ- ሰርቪስ... read more
ምላሽ ይስጡ