ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)አገልግሎቱ 100 የከባድ ጭነት ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆኑንም ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ሀገሪቱ የደረሰችበትን የዕድገት ደረጃ የሚመጥን የከባድ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት ለመዘርጋት የ5 ዓመት ዕቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነም ይታወቃል፡፡
የአገልግሎቱ የማርኬቲንግ መምሪያ ኃላፊና ተወካይ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደምሰው በንቲ፤ በመርከብ፣ በከባድ ተሽከርካሪዎችና በሌሎችም ዘርፎች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ታቅዶ በዚህ ዓመት ብቻ 100 የከባድ ተሽከርካሪዎችን በመግዛት አጠቃላይ ቁጥሩን ወደ 6 መቶ 52 ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ የወደብ ፍላጎቷን ለማሟላት በርካታ ሥራዎችን እየሠራች ባለችበት በአሁኑ ወቅት፤ ፈጣን፣ ዘመናዊና በተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮች የተሳሰሩ አሰራሮችን መዘርጋት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ አሁን ላይ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚያስችል መልኩ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ለማስገባት በሂደት ላይ መሆናቸውን አቶ ደምሰው ተናግረዋል፡፡
የባህር ትራንስፖርት ዘርፉ በሰው ሀብት ማብቃት፣ በዘመናዊ አሠራርና በመሣሪያ አቅርቦት ረገድ በሚጠበቀው ልክ አይደለም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ እነዚህን ክፍተቶች ለማሟላት የ5 ዓመት ዕቅድ ተነድፎ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠትና አሠራሩን ለማቀላጠፍ በርካታ የማሻሻያ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ለኬሚካል ርጭት አገልግሎት በግብርና ሚኒስቴር በኩል የተገዙት 5 አዉሮፕላኖችን መከራየት የሚፈልጉ ሃገራት ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑ ተገለጸ
ታኅሳስ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቅርቡ ለኬሚካል ርጭት አገልግሎት የሚውሉ 5 የአውሮፕላን ግዢ መፈፀሙን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስታወቀ ሲሆን 10... read more
ከ152 ሺህ በላይ የደንብ መተላለፎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱ ተገለጸ
ጥር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከ27 ተቋማት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር... read more
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ምላሽ እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ውጤትን በተመለከተ በተማሪዎች የሚቀርቡ ቅሬታዎች ታይተው ምላሽ... read more
ከመጋቢት ወር ጀምሮ በከተማዋ ወደ 28 የሚደርሱ ሆቴሎች እና ሬስቶራንቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ተባለ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከመጋቢት ወር ጀምሮ ደንብ እና መመሪያ ተላልፈዋል የተባሉ ወደ 28 የሚጠጉ ሆቴሎች ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው፣ የከተማ አስተዳደሩ... read more
የብሄራዊ ባንክ እና የኢትዮጵያ ኦዲት ቦርድ አገልግሎታቸውን የጨረሱ ሰነዶች እንዲወገዱ መደረጉ ተገለጸ
የብሄራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ኦዲት ቦርድ አገልግሎታቸውን የጨረሱ ሰነዶች እንዲወገዱ መደረጉን የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፅሀፍት አገልግሎት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
አገልግሎቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት... read more
አሜሪካና ቻይና ቲክቶክን ተከትሎ በምን ጉዳዮች ላይ ተስማሙ?
መስከረም 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካና የቻይና መንግስታት በቻይናው ኩባንያ ByteDance ስር ባለው ታዋቂው የቪዲዮ መጋሪያ መተግበሪያ ቲክቶክ ዙሪያ... read more
የሞባይል አፕሊኬሽኖች የሳይበር ወንጀለኞች ሰፊ ኢላማ እየሆኑ ነው ተባለ
የሞባይል መተግበሪያዎች (ሞባይል አፕሊኬሽኖች) የግል መረጃዎችን በስፋት በመያዛቸው የሳይበር ወንጀለኞች ዋነኛ ኢላማ እየሆኑ መምጣታቸውን የዘርፉ ባለሙያዎች አስጠነቀቁ።
በተለይም የአይኦኤስ (iOS) ስልኮች... read more
በትግራይ ክልል የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች ወደ ጦርነት እንዳይገቡ ቅስቀሳ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች በተለያዩ ምክንያቶች ተገፋፍተው ወደ ጦርነት እንዳይገቡ ቅስቀሳ እያደረገ መሆኑን ስምረት... read more
የዓለማችን ብቸኛዋ ሰው አልባ አህጉር አንታርክቲካ
ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአለማችን ላይ ብቸኛዋ ቋሚ ነዋሪ የሌላት አህጉር አንታርክቲካ መሆኗ ተገለጸ። ይህች በበረዶ የተሸፈነች አህጉር ምንም እንኳን... read more
3 ሺህ 285 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 285 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 2747... read more
ምላሽ ይስጡ