ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሥራ እንዲጀምሩ አዋጅ መዘጋጀቱን ተከትሎ፣ የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት እንዳይዳከሙ መጠናከር እንደሚገባቸው በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማት ለጣቢያችን ገልጸዋል።
በአገር ውስጥ ያለው የፋይናንስ አሠራር እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ አገር በቀል የሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ማደግ በሚገባቸው ልክ እንዳያድጉ ማድረጉን የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የኢንተርፕራይዝ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ ፍሥሐ ተስፋዬ ገልጸዋል። በአንጻሩ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ የተሰማሩ ተቋማት በጋራና በጥምረት ሊሠሩባቸው የሚችሉ ጉዳዮችን በመለየት ማጠናከር እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ በርካታው የማኅበረሰብ ክፍል የሚገኘው በአገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች ላይ እንደመሆኑ፣ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ የኅብረት ሥራ ተቋማት አቅማቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የኢንፊኒቲ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ሥራ ተቋም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እስክንድር መኩሪያ ይገልጻሉ። በተለይም ደግሞ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ የሚስተዋለው የትብብር ማነስ፣ የጥሬ ገንዘብ እጥረትና ተደራሽነት፣ እንዲሁም ጠንካራ ተቋማት ጥቂት መሆን ሊሻሻሉ የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሥራ መጀመራቸው ለትልልቅ የኢንቨስትመንት ሥራዎች እና ለውጭ ምንዛሬ አቅርቦት በጎ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል። ከሰሞኑ በኢንቨስትመንት ባንክ ሥራ ላይ የተሰማራው የናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ በካፒታል ገበያ ላይ ሕጋዊ ፈቃድ ያገኘ ሲሆን፣ በቀጣይም በኢትዮጵያ በባንክ አገልግሎት ዘርፍም ሆነ በኢንሹራንስ ዘርፍ የተሰማሩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ፈቃድ አግኝተው ሥራ ሲጀምሩ ለኢኮኖሚው ጠቃሚ እንደሚሆኑና በአገር በቀል ባንኮች ላይ ጫና እንደማያሳድሩ አመላክተዋል።
የውጭ አገር ባንኮች በአገር ውስጥ ገብተው እንዲሠሩ የሚፈቅደው አዋጅ መጽደቁ የሚታወስ ሲሆን፣ የኢንሹራንስ ድርጅቶች እንዲሠሩ የሚፈቅደው ረቂቅ አዋጅም በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በሸዋሮቢት ከተማና አካባቢው አጥፊው የግሪሳ ወፍ በመከሰቱ ምክንያት አስቸኳይ የኬሚካል ርጭት ሊካሄድ ነው
መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም. (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ግብርና ፅህፈት ቤት በቀጠናው አጥፊው የግሪሳ ወፍ መከሰቱን አስታወቀ። ፅህፈት... read more
የዐረብ ሴቶች ልብስ ለብሰው ለመብረር ሲሞክሩ የተያዙ ሶስት ወንዶች ታሪክ መነጋገሪያ ሆኗል
ጥቅምት 13 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአልጄሪያ የአውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሦስት ተጠርጣሪ ወንዶች ታሪክ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ መነጋገሪያ... read more
በጥበብ ስራ ላይ የሚሳተፉ ተዋንያን የተሰጣቸዉን ሙያን የተመለከቱ ገጸ ባህሪያት በተገቢዉ መንገድ መወጣት እንዲችሉ ስልጣና እና ጥናት ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ
ፊልም ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ ተሰጥዖን የሚጠይቅ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ ያንን ገጸባህሪ ወክለዉ የሚጫወቱባቸዉ የተለያዩ አይነት ዘርፎች በትክክል መላበስ... read more
በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ዜጎች ከጸጥታ ችግር ባለፈ በህክምና ግብዓት አቅርቦት እጥረት ምክንያት የከፋ ቀውስ ውስጥ ናቸው ተባለ
ባለፉት 5 ዓመታት በአገራችን የተለያዩ አከባቢዎች በሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት የበርካቶች ህይወት ማለፉ፤ ንብረት መውደሙ እና የበዙትም ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን... read more
እንደ ሀገር ይህ ነው ተብሎ የተለየ ስያሜ የሚሰጠው የኢኮኖሚ ርዕዮት ዓለም እንደሌለ ተገለጸ
ኅዳር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሁን ላይ እንደ ሀገር የምንከለተው የኢኮኖሚ ስርዓት አፈጻጸሙና መልኩ ካፒታሊስት ይምሰል እንጂ ቅይጥ ኢኮኖሚ፣ ካፒታሊስት... read more
የዓለም ኃያላን በንፅፅር፡ ቻይና ወይስ ዩኤስ? (በጀት፣ አውሮፕላን እና ኑክሌር)
ሕዳር 10 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የዓለምን ጂኦፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምህዳር የሚመሩት ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ በተለያዩ ቁልፍ ዘርፎች ያላቸው ብቃት... read more
የእናት ፍቅር ኃይል፡ የሞተ ግልገሏን ከ1,600 ኪሎሜትር በላይ የተሸከመችው ኦርካ
👉በሳይንቲስቶች ዘንድ የሐዘን መግለጫ ተብሎ የተፈረጀው የኦርካዋ ታሪክ
ጥቅምት 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በእንስሳት ዓለም ውስጥ በእናትና በልጅ መካከል ያለውን ልዩ ትስስር... read more
የውጭ ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ መቀዛቀዝ በሴቶችና በእናቶች ላይ የሚሰሩ ስራዎቸን ፈትኗል ተባለ
ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተያዘው በጀት አመት በአለም አቀፍ ደረጃ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ የተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ መቀዛቀዝ በሴቶችና... read more
“ባለመመካከራችን ብዙ ዋጋ ከፍለናል፤ እንመካከር”👉 ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕሮፌሰር)
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕሮፌሰር) ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት ዛሬ መጋቢት 27/2017 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የተጀመረውን... read more
የማዳጋስካር ፕሬዚዳንት ከሀገር ሸሹ፤ ወታደራዊ ክፍሎች ተቃዋሚዎችን ተቀላቀሉ!
ጥቅምት 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በማዳጋስካር እየተባባሰ የመጣውን የፖለቲካ ቀውስ ተከትሎ፣ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ከስልጣናቸው በመልቀቅ ከሀገር መውጣታቸው ተዘገበ። ፕሬዚዳንቱን ለቀው እንዲሸሹ... read more
ምላሽ ይስጡ