ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሥራ እንዲጀምሩ አዋጅ መዘጋጀቱን ተከትሎ፣ የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት እንዳይዳከሙ መጠናከር እንደሚገባቸው በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማት ለጣቢያችን ገልጸዋል።
በአገር ውስጥ ያለው የፋይናንስ አሠራር እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ አገር በቀል የሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ማደግ በሚገባቸው ልክ እንዳያድጉ ማድረጉን የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የኢንተርፕራይዝ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ ፍሥሐ ተስፋዬ ገልጸዋል። በአንጻሩ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ የተሰማሩ ተቋማት በጋራና በጥምረት ሊሠሩባቸው የሚችሉ ጉዳዮችን በመለየት ማጠናከር እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ በርካታው የማኅበረሰብ ክፍል የሚገኘው በአገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች ላይ እንደመሆኑ፣ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ የኅብረት ሥራ ተቋማት አቅማቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የኢንፊኒቲ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ሥራ ተቋም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እስክንድር መኩሪያ ይገልጻሉ። በተለይም ደግሞ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ የሚስተዋለው የትብብር ማነስ፣ የጥሬ ገንዘብ እጥረትና ተደራሽነት፣ እንዲሁም ጠንካራ ተቋማት ጥቂት መሆን ሊሻሻሉ የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሥራ መጀመራቸው ለትልልቅ የኢንቨስትመንት ሥራዎች እና ለውጭ ምንዛሬ አቅርቦት በጎ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል። ከሰሞኑ በኢንቨስትመንት ባንክ ሥራ ላይ የተሰማራው የናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ በካፒታል ገበያ ላይ ሕጋዊ ፈቃድ ያገኘ ሲሆን፣ በቀጣይም በኢትዮጵያ በባንክ አገልግሎት ዘርፍም ሆነ በኢንሹራንስ ዘርፍ የተሰማሩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ፈቃድ አግኝተው ሥራ ሲጀምሩ ለኢኮኖሚው ጠቃሚ እንደሚሆኑና በአገር በቀል ባንኮች ላይ ጫና እንደማያሳድሩ አመላክተዋል።
የውጭ አገር ባንኮች በአገር ውስጥ ገብተው እንዲሠሩ የሚፈቅደው አዋጅ መጽደቁ የሚታወስ ሲሆን፣ የኢንሹራንስ ድርጅቶች እንዲሠሩ የሚፈቅደው ረቂቅ አዋጅም በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በአዋሽ ፈንታሌ እየወጣ ያለው የጋዝ መጠን እየጨመረ መሆኑን ተከትሎ ለአደጋ ተጋላጭ ናቸው የተባሉ 60ሺሕ ዜጎች በክልሉ በሚገኙ የአይ.ሲ.ቲ ፖርኮች እንዲሰፍሩ እየተደረገ ነው ተባለ
በአፋር ክልል ፈንታሌ ባልተለመደ መልኩ እየወጣ ያለው ሚቴን ጋዝ ከእሳተ ጎመራ ጋር ሊያያዝ ብሎም በአከባቢው የአየር ፀባይ ላይ ለውጥ ሊያመጣ... read more
በተመረጡ ስድስት ዘርፎች 5ኛው የጣፋጭ ህይወት የምስጋና መርሃ-ግብር ሊካሄድ ነዉ
በተመረጡ 6 ዘርፎች ላይ 5ኛው የጣፋጭ ህይወት የምስጋና መርሃ-ግብር ሊካሄድ መሆኑን ጣፋጭ ህይወት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
በየአመቱ እየተከናወነ ያለዉ... read more
በጦርነት የሚመጣ መፍትሔ ባለመኖሩ ሁሉም ለሠላም በሩን እንዲከፍት ጥሪ ቀረበ
ነሐሴ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት የሚያጋጥሙ የሠላም መደፍረሶችን ለመፍታት የተለያየ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር... read more
ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለትግራይ ልማት ማህበር የተሰጠ ማሳሰቢያ
ሙሉ መግለጫው ከታች ተያይዟል
ጉዳዩ፡ ማህበሩ በቅርቡ ያካሄደው ጉባኤን ይመለከታል
የትግራይ ልማት ማህበር (ትልማ) በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በመዝገብ... read more
ግንባታቸው ከ80 በመቶ በላይ ያልተጠናቀቁ ሪል እስቴቶች ለሽያጭ እንደማይቀርቡ ተገለጸ
ኅዳር 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ የህንፃ አዋጅን ለማፅደቀ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ... read more
ቴሌግራም የተጠቃሚዎችን ደኅንነት በተመለከተ የአቋም ለውጥ አደረገ
ኅዳር 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተጠቃሚያቸው እያደገ ከሚገኙት የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መተግበሪያዎች መካከል አንዱ የሆነው ቴሌግራም ሲወቀስበት የነበረውን የተጠቃሚዎች ደኅንነት... read more
በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ ምክር ቤት ውሳኔ ሰጪ መሆኑ ከዚህ ቀደም ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ነዉ ተባለ
በትግራይ ክልል ከሳምንታት በፊት የተቋቋመው ጊዜያዊ አማካሪ ካውንስል መፍረሱን እና እሱን የሚተካ ጊዜያዊ ምክር ቤት መቋቋሙ ተገልጿል፡፡ ከ2 ሳምንታት... read more
57ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 57ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው ከዓለም... read more
የዓለም የህዝብ ብዛት ምን ያክል ነው?
👉የወንዶች ቁጥር ከሴቶች ይበልጣል?
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዛሬው ዕለት ባለው መረጃ መሰረት የዓለም ህዝብ ብዛት ከ8.1 ቢሊዮን በላይ ደርሷል።... read more
♻️የፕሮግራም ማስታወሻ
ቅዳሜ ጥር 01 ቀን 2017 ዓ.ም በመናኸሪያ እንግዳ ፕሮግራማችን የወጋገን ባንክ ፕሬዝደንት አክሊሉ ወበት ዶ/ር እንግዳችን በመሆን የህይወት ተሞክሮና ልምዳቸውን... read more
ምላሽ ይስጡ