ሰኔ 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) አለም በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው ታላቅ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት እውን ሆኗል! በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ለወራት የዘለቀውን አስከፊ ግጭት እና ወታደራዊ ውጥረትን በይፋ የሚቋጨው ባለ 14 ነጥብ ታሪካዊ የሰላም ስምምነት (MoU) በፈረንሳዩ ታዋቂ የቫርሳይ ቤተ-መንግስት (Palace of Versailles) ውስጥ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እጅ በይፋ ተፈርሟል። በፈረንሳይ አስተናጋጅነት በተካሄደው የጂ7 (G7) ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት አማኑኤል ማክሮን ባዘጋጁት ልዩ የራት ግብዣ ላይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሰነዱን በፊርማቸው ካጸደቁ በኋላ “ይህ ቀላል አልነበረም” ሲሉ ለታዳሚው ተናግረዋል።
ከኢራን በኩል ደግሞ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን (Masoud Pezeshkian) ስምምነቱን በዲጂታል መንገድ የፈረሙ ሲሆን፣ ይህ ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረውን ወታደራዊ ግጭት በአስቸኳይ የሚያቆምና በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቀውስ ፈጥሮ የነበረውን የሆርሙዝ ባህረ-ሰላጤ (Strait of Hormuz) ለነዳጅ ማመላለሻ መርከቦች ክፍት የሚያደርግ ነው። ፈረንሳይ ለዚህ ታሪካዊ ስምምነት ማደሪያ እንዲሆን የመረጠችው የቫርሳይ ቤተ-መንግስት፣ አንደኛውን የአለም ጦርነት ጨምሮ በርካታ ታላላቅ የአለም የሰላም ውሎችን ያስተናገደ በመሆኑ የስምምነቱን ታላቅነት የበለጠ አጉልቶታል።
ይህ ስምምነት አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን የነዳጅ ማዕቀብ ወዲያውኑ እንድታነሳና ለሀገሪቱ መልሶ ግንባታ የሚውል የ$300 ቢሊዮን ፈንድ እንዲመቻች መንገድ የሚከፍት በመሆኑ፣ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከራት ግብዣው ሲወጡ ለተሰበሰቡት ጋዜጠኞች ስምምነቱ መፈረሙን በኩራት ያረጋገጡ ሲሆን፣ ይህ ዲፕሎማሲያዊ ውሳኔ በአለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ በማምጣት ለተጠቃሚዎች ትልቅ እፎይታን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ