ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ማንቸስተር ዩናይትድ የቶተንሃሙን አምበል ክሪስቲያን ሮሜሮን ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ እያዘጋጀ መሆኑ ተዘግቧል።
የ28 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ተከላካይ ቶተንሃም በፕሪሚየር ሊጉ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት 17ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ተከትሎ፣ በዚህ ክረምት ክለቡን ይለቃል ተብሎ በስፋት ይጠበቃል። አርጀንቲናዊው ጋዜጠኛ ጋስተን ኤዱል እንደዘገበው፤ ማንቸስተር ዩናይትድ ቀጣዩ የተጫዋቹ ማረፊያ ለመሆን ተስፋ በማድረግ ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ይገኛል።
ጊቭሚስፖርት (GiveMeSport) በበኩሉ፣ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ሮሜሮን አሁንም የቡድኑ ወሳኝ አካል አድርጎ ስለሚመለከተው በቀላሉ አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑን ገልጿል። የ2022 የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ሮሜሮ፣ ክለቡ ቶተንሃም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም እንኳ ራሱን በፕሪሚየር ሊጉ ካሉ ምርጥ የመሀል ተከላካዮች አንዱ ማድረግ በመቻሉ፣ ቶተንሃሞች ለዝውውሩ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን እንደሚጠይቁ ይገመታል።
የትራይባል ፉትቦል (Tribal Football) ዘጋቢው አሌክስ ሮበርትስ በበኩሉ፤ ሮሜሮ በቶተንሃም ያለው የኮንትራት ውል ማፍረሻ 50 ሚሊዮን ዩሮ መሆኑንና ይህንን ገንዘብ ለማቅረብ ዩናይትድ ዝግጁ መሆኑን ገልጾ፤ ተጫዋቹን ከአገሩ ልጅና ከቅርብ ጓደኛው ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ጋር የማጣመር ዕቅድ እንዳላቸው ዘግቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ ጥያቄ ተጠቃሚ ለመሆን በርካታ የቤት ስራዎች ይጠብቋታል ተባለ
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ ለማግኘት በምታደርገው እንቅስቃሴ በኩል ተጠቃሚ ለመሆን በርካታ የዲፕሎማሲ ስራዎች ይጠበቁባታል ሲሉ ለመናኸሪያ... read more
አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ላይ ክፍተቶች እንዳሉባቸው ተገለጸ
ሰኔ 19 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሥነ-አእምሮ ሕክምና ሥራም ሆነ በትምህርት ሂደት ውስጥ “ችግር አለበት” ተብሎ የሚገለል ልጅ ሊኖር እንደማይገባ የገለጹት... read more
በጀልባ መስጠም አደጋ የ20 ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፈ
ጥር 14 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ጥር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ቅዳሜ ምሽት ላይ 35 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከየመናዊ ካፒቴን እና... read more
ከውጭ እርዳታ ጥገኝነት ለመላቀቅ የመከረው የምስራቅ አፍሪካ የበጎ አድራጎት ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጠናቀቀ
ሰኔ 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከ30 በላይ ሀገራትን የወከሉ ከ600 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙበት 10ኛው የምስራቅ አፍሪካ የበጎ አድራጎት ጉባኤ ከውጭ... read more
በሰሜን ዋዚሪስታን በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት 13 የጸጥታ ኃይሎች ሲሞቱ 14 ንፁሃን ቆስለዋል
ሰኔ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በፓኪስታን ሰሜናዊ ምዕራብ በሚገኘው ሰሜን ዋዚሪስታን ክልል ውስጥ በተፈጸመ ከባድ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት 13... read more
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ገቡ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ በደረሱበት ወቅት በፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር... read more
ዝምተኛው ማዕበል በሚል የሚጠራው የፀረ- ተዋሲያን በጀርሞች መለመድ በሰዎች ላይ ያስከተለው ውስብስብ ችግር 👉
https://youtu.be/LRBdqWz6Eio
read more
የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት በ5 ዘርፎች ተዘጋጅተው ከቀረቡለት 63 ደረጃዎች 34ቱን ማፅደቁ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በ5 ዘርፎች ተዘጋጅተው ከቀረቡለት 63 አስገዳጅ እና ሌሎችም የኢትዮጵያ ደረጃዎች 34ቱን ማፅደቁን የኢንስቲትዩቱ... read more
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ለመጀመሪያ ጊዜ 39.5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን ገለጸ
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተቋሙ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 96.5 ቢሊዮን ብር ማትረፉን የሃይሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ... read more
በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ይቆማል የሚል ግምት እንደሌለ ተገለጸ
ታኅሳስ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሁን ላይ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ይቆማል የሚል ግምት እንደሌለ የገለጹት የዘርፉ ባለሙያዎች ናቸው፡፡
መንቀጥቀጡ... read more
ምላሽ ይስጡ