ሰኔ 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓለማችን ላይ የመደበኛ ቴሌቪዥን ስርጭት (Broadcast TV) ዘመን በፍጥነት እያከተመለት መሆኑንና የዜና ፍጆታ ወደ ማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ሙሉ በሙሉ እየተቀየረ መሆኑን አዲስ የወጣ ዓለም አቀፍ ጥናት አመለከተ።
የሬውተርስ ኢንስቲትዩት (Reuters Institute) ይፋ ባደረገው የ2026 የዲጂታል ዜና ሪፖርት መሠረት፣ በተለይ ወጣቱ ትውልድ መደበኛ የዜና ስርጭቶችን ሙሉ በሙሉ እየተወ ሲሆን፣ የዜና ተቋማት የገዛ ድረ-ገጾች እና መተግበሪያዎችም (Apps) ከተጠቃሚዎች እይታ ውጪ እየሆኑ መጥተዋል።
🚨 ቁልፍ እና አስገራሚ ግኝቶች፦
የአፍሪካውያን አስደናቂ ተሳትፎ፦ በኦንላይን ቪዲዮ ዜና ፍጆታ አፍሪካ፣ ላቲን አሜሪካ እና ደቡብ ምስራቅ እስያ ዓለማችንን እየመሩ ይገኛሉ። በአፍሪካ 54% የሚሆነው ማህበረሰብ ዜናን በYouTube የሚከታተል ሲሆን፣ በአውሮፓ ግን ይህ ቁጥር 24% ብቻ ነው። በአጠቃላይ በታይላንድ እና ደቡብ አፍሪካ ከ80% በላይ ህዝብ ዜናን በኦንላይን ቪዲዮ ያያል።
👉TikTok እና Instagram የዜና መናኸሪያ ሆነዋል፦ ዕድሜያቸው ከ18-24 የሆኑ ወጣቶች ዜናን ፈልገው ከማንበብ ይልቅ፣ በቲክቶክ እና ኢንስታግራም ላይ ተከታታይ የሆኑ ከ2 ደቂቃ በታች አጫጭር ቪዲዮዎችን (Short-form videos) በአጋጣሚ መመልከትን መርጠዋል።
👉የረዣዥም ቪዲዮዎች ማዕከል
YouTube፦ ወጣቶች አጫጭር ቪዲዮዎችን ይውደዱ እንጂ፣ ጥልቅ መረጃዎችን ለማግኘት እስከ 20 ደቂቃ የሚረዝሙ የYouTube ቪዲዮዎችን ፈልገው (የመመልከት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው በጥናቱ ተረጋግጧል።
🔰የስማርት ቲቪ (Smart TV) አብዮት፦ ሰዎች ቴሌቪዥን ማየት አላቆሙም፤ ነገር ግን አጠቃቀማቸው ተቀይሯል። ከ45 ዓመት በታች የሆኑ 70% የሚጠጉ የቪዲዮ ተጠቃሚዎች ቴሌቪዥናቸውን የሚከፍቱት መደበኛ ጣቢያዎችን ለመመልከት ሳይሆን እንደ YouTube እና Netflix ያሉ መተግበሪያዎችን (Apps) ለመጠቀም ነው።
🎯 የዜና ተቋማት ህልውና አደጋ ላይ?
ሪፖርቱ በጥብቅ እንዳሳሰበው፣ ባህላዊ የዜና ማሰራጫዎች (የቴሌቪዥንና ጋዜጣ ተቋማት) ከቲክቶክ፣ ኢንስታግራም እና ዩቲዩብ የይዘት ፈጣሪዎች (Influencers/Creators) ጋር መፎካከር አቅቷቸዋል። ከተመልካች ፍላጎት ጋር በአስቸኳይ የማይራመዱ የዜና ተቋማት በቀጣዮቹ ዓመታት ሙሉ በሙሉ የመክሰም አደጋ ተጋርጦባቸዋል ሲል የሬውተርስ ኢንስቲትዩት የ2026 የዲጂታል ዜና ሪፖርት አመላክቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ