ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ማንቸስተር ዩናይትድ የቶተንሃሙን አምበል ክሪስቲያን ሮሜሮን ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ እያዘጋጀ መሆኑ ተዘግቧል።
የ28 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ተከላካይ ቶተንሃም በፕሪሚየር ሊጉ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት 17ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ተከትሎ፣ በዚህ ክረምት ክለቡን ይለቃል ተብሎ በስፋት ይጠበቃል። አርጀንቲናዊው ጋዜጠኛ ጋስተን ኤዱል እንደዘገበው፤ ማንቸስተር ዩናይትድ ቀጣዩ የተጫዋቹ ማረፊያ ለመሆን ተስፋ በማድረግ ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ይገኛል።
ጊቭሚስፖርት (GiveMeSport) በበኩሉ፣ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ሮሜሮን አሁንም የቡድኑ ወሳኝ አካል አድርጎ ስለሚመለከተው በቀላሉ አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑን ገልጿል። የ2022 የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ሮሜሮ፣ ክለቡ ቶተንሃም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም እንኳ ራሱን በፕሪሚየር ሊጉ ካሉ ምርጥ የመሀል ተከላካዮች አንዱ ማድረግ በመቻሉ፣ ቶተንሃሞች ለዝውውሩ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን እንደሚጠይቁ ይገመታል።
የትራይባል ፉትቦል (Tribal Football) ዘጋቢው አሌክስ ሮበርትስ በበኩሉ፤ ሮሜሮ በቶተንሃም ያለው የኮንትራት ውል ማፍረሻ 50 ሚሊዮን ዩሮ መሆኑንና ይህንን ገንዘብ ለማቅረብ ዩናይትድ ዝግጁ መሆኑን ገልጾ፤ ተጫዋቹን ከአገሩ ልጅና ከቅርብ ጓደኛው ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ጋር የማጣመር ዕቅድ እንዳላቸው ዘግቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
42ኛው የሻምበል አበበ በቂላ ማራቶን የፊታችን እሁድ በሀዋሳ ከተማ በድምቀት ይካሄዳል
ሰኔ 18 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) 42ኛው የሻምበል አበበ በቂላ ማራቶን የፊታችን እሁድ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና ሀዋሳ ከተማ በድምቀት... read more
የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ መሳሪያ አንግበው ግጭት ውስጥ ያሉ ቡድኖች በአገራዊ ምክክሩ የአጀንዳ ማሰባሰብ እንዲሳተፉ ኮሚሽኑ ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረቡን እንደሚቀጥል ገልጿል
ታኅሳስ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኦሮሚያ ክልል ሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ በአዳማ ከተማ መካሄዱን ቀጥሏል፡፡
ከክልሉ 356 ወረዳዎች የተመረጡ ከ7... read more
የኢራን ፎርዶው የዩራኒየም ማበልጸጊያ ተቋም ጥገና ሥራ ሲከናወን የሚያሳዩ አዳዲስ የሳተላይት ምስሎች ይፋ ሆኑ
ሰኔ 23 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በእስራኤል እና በዩናይትድ ስቴትስ የአየር ጥቃቶች ጉዳት ደርሶበት በነበረው የኢራን ፎርዶው የዩራኒየም ማበልጸጊያ ተቋም... read more
ቤተሰብን ለመደገፍ በሚሰራው ስራ የመዋቅርና የፖሊሲ ማዕቀፍ ችግር መኖሩ ተገለጸ
ቤተሰብን በመደገፍ ስራ ውስጥ የመዋቅርና የፖሊሲ ማዕቀፍ ችግር መኖሩን ለጣቢያችን የገለጸው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።
ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የቤተሰብ ህጎችን... read more
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ55ኛ መደበኛ ስብሰባው በርካታ ረቂቅ አዋጆችን፣ ፖሊሲዎችንና ደንቦችን አጸደቀ
ግንቦት 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሚኒስትሮች ምክር ቤት ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው 55ኛ መደበኛ ስብሰባው ሀገራዊ ኢኮኖሚን፣ ማኅበራዊ ልማትንና... read more
በሱዳን ዳርፉር ክልል በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ1,000 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሱዳን ምዕራባዊ ዳርፉር ክልል ውስጥ በመራ ተራሮች አካባቢ ታራሲን በተባለች መንደር ላይ በደረሰ ከባድ የመሬት... read more
የኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ሥራ ማኅበር ለሴቶች የተሻሉ የብድር አማራጮችን ይፋ አደረገ
ሰኔ 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዋጅ ቁጥር 985/09 መሠረት በ2017 ዓ.ም የተቋቋመው ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ሥራ ማኅበር፣ ለሴቶች... read more
የደቡብ አፍሪካ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በእንግሊዝ መንግስት ቪዛ መከልከላቸውን ተቃወሙ
የኢኮኖሚ ፍሪደም ፋየርስ ፓርቲ መሪ ጁሊየስ ማሌማ በእንግሊዝ ሊያደርጉት የነበረው ጉብኝት በቪዛ ምክንያት ከጉዞ መታገዳቸውን መርህ አልባ ሲሉ ተችተውታል።
የምዕራባውያን ኢምፔሪያሊዝም... read more
በሀገሪቱ በነዳጅ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎች ወደ ጋዝ ተጠቃሚነት ይቀየራሉ መባሉ ሀገሪቱ በከፍተኛ ድጎማ በምታስገባው የነዳጅ ምርት ላይ አንፃራዊ ለውጥ ያመጣል ተባለ
መስከረም 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህንን ያለው የኢትዮጵያ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ነው። ከሰሞኑ የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ... read more
የማስተርስ ትምህርት የቆይታ ጊዜ እንደሚጨምር ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑ ተገለጸ
ሰኔ 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሁለተኛ ዲግሪ (Master's Degree) የትምህርት ቆይታ ጊዜ ወደ አራት ዓመት ሊያድግ ነው በሚል በተለያዩ... read more
ምላሽ ይስጡ