ግንቦት 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰውን ልጅ ወደ ማርስ እና ጨረቃ ለማጓጓዝ እንዲሁም በህዋ ላይ በቋሚነት ለማስፈር ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍ የተሻገረበት አስገራሚ ሙከራ ተደረገ። የቻይና ሳይንቲስቶች የሰው ልጅ በህዋ ላይ መባዛት (Human Reproduction) የሚችል መሆኑን እና አለመሆኑን በጥልቀት ለማጥናት በጥናት ላይ የተመሰረቱ ሰው ሰራሽ የሰው ልጅ ሽሎችን (Artificial Embryo Models) ወደ ቲያንጎንግ የጠፈር ጣቢያ ልከዋል።
ከግንድ ሴል (Stem Cell) የተሰሩት እነዚህ የሽል ሞዴሎች የሰው ልጅ ከተረገዘ ከ14 እስከ 21 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚያሳየውን እጅግ የመጀመሪያ ደረጃ የዕድገት ሂደት ሙሉ በሙሉ መኮረጅ የሚችሉ ናቸው። ሆኖም ግን እነዚህ ሞዴሎች ወደ እውነተኛ የሰው ልጅ ፅንስ ወይም ሙሉ ሰውነት ሊያድጉ የማይችሉ በመሆናቸው ምንም ዓይነት የስነ-ምግባር ጥያቄ እንደማያስነሱ ተመራማሪዎቹ አረጋግጠዋል።
ሳይንቲስቶቹ በዚህ ሙከራ በህዋ ላይ ያለው አነስተኛ የስበት ኃይል እና የኮስሚክ ጨረራ በሰው ልጅ የሴል ዕድገት፣ በጂን መገለጫዎች እና በውስጥ አካላት አወቃቀር ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለማወቅ ፈልገዋል።
ይህ ታሪካዊ ሙከራ ወደ ጠፈር የተላከው በቅርቡ በተኮሰችው ቲያንዙ-10 (Tianzhou-10) በተባለችው የጭነት መንኮራኩር አማካኝነት ሲሆን፣ ሙከራው እየተመራ ያለው በቻይና የሳይንስ አካዳሚ የስነ-ሕይወት ተቋም (Chinese Academy of Sciences’ Institute of Zoology) አማካኝነት ነው።
ሳይንቲስቶች እንዳረጋገጡት ይህ ሽል በህዋ ላይ እንዴት እንደሚንቀሳቀስና እንደሚያድግ የሚታወቅበት ሚስጥር፣ የሰውን ልጅ ወደፊት በጠፈር ጣቢያዎች ወይም በሌሎች ፕላኔቶች ላይ በቋሚነት ለማስፈርና አዳዲስ ቅኝ ግዛቶችን ለመመስረት ለሚደረገው ጉዞ እጅግ ወሳኝና የመጨረሻው ቁልፍ መረጃ ሆኖ ያገለግላል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በመዲናዋ 10 የሚሆኑ ፏፏቴዎች ቢኖሩም ለቱሪስት ሳቢ ለማድረግ ጥናት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
በከተማዋ ባሉት ፏፏቴዎች የቱሪስቶችን ቀልብ የሚስቡ አድርጎ ለማስቀጠል የማልማት ስራ እየተሰራ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት... read more
“በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ ሙሉ ቁጥጥር አለን፤ ኢራንን በፍጹም አላምንም!” – ዶናልድ ትራምፕ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በስትራቴጂካዊው የሆርሙዝ ሰርጥ የባህር መስመር ላይ "ሙሉ ቁጥጥር" እንዳላት በመግለጽ በኢራን ላይ የሰነዘሩትን ጠንካራ ወቀሳ... read more
የሞት ቅጣትን የሚተገብሩ ሃገራት
የሞት ቅጣት አሁንም በበርካታ የዓለም ሀገራት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግ የቅጣት አይነት ነው። ምንም እንኳን አብዛኞቹ ሀገራት የሞት ቅጣትን ሙሉ በሙሉ... read more
የምድር ህልውና አደጋ ላይ ነው
🔰ሳይንሳዊ ግኝቶች ምን ይላሉ?
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ናሳ እና ቶሆ ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት የቅርብ ጊዜ ጥናት፣ ምድር ለዘለቄታው የመኖሪያ ምቹነት... read more
“የአደጋ ጊዜ ትምህርት” ለመስጠት ብዘጋጅም በዘርፉ ሰልጣኞችን ማግኘት አልቻልኩም ሲል የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ገለጸ
ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በ2017 የትምህርት ዘመን በ2ተኛ ዲግሪ /ማስተርስ ደረጃ/ ለመስጠት ያዘጋጀው የአደጋ ጊዜ ስርዓተ... read more
የቴኳንዶ ስፖርት በበጀት ችግር ምክንያት የታሰበውን ያህል እያደገ አለመሆኑ ተገለጸ
እንደ ሀገር ህብረተሰቡ እንዲሁም ስፖርቱን ከመንግስት በተጨማሪ ይደግፋሉ ተብለዉ የሚታሰቡ ባለሀብቶች ስለ ቴኳንዶ ስፖርት ግንዛቤው ስለሌላቸው ተደጋጋሚ የበጀት እጥረት እንዲገጥመው... read more
በትግራይ ክልል የጤና መድህን አገልግሎት ለማስጀመር በሚደረገው የቅድመ ዝግጅት ስራ በክልሉ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ተጽዕኖ እየፈጠረ መሆኑ ተገለጸ
በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት የጤና መድህን አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር መገለጹ ይታወቃል።
የተቋረጠውን አገልግሎት ዳግም ለማስጀመር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ... read more
የአይ ኤም ኤፍ ዳይሬክተሯ ስለ ኢትዮጵያ አዎንታዊ ሀሳብ ማንሳታቸው ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ሀገሪቱን ተመራጭ እንዲያደርጉ እድል የሚሰጥ ነዉ ተባለ
የአይ ኤም ኤፍ ዳይሬክተሯ ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ዳሬክተሯ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ለመገናኛ... read more
በመዲናዋ ሰርግን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ የሚፈጽሙ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል👉ፖሊስ
በአዲስ አበባ ከተማ በዓላትና ሰርግን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ የሚፈጽሙ መንገድ የሚዘጉ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ።
ሕብረተሰቡ... read more
አሌክሳንደር ኢሳክ ከ4 ወራት ቆይታ በኋላ ወደ ሜዳ መመለሱን ክለቡ አስታውቋል
መጋቢት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሊቨርፑል በ125 ሚሊዮን ፓውንድ የእንግሊዝ የዝውውር ክብረ ወሰንን በመስበር ያስፈረመው፣ ትውልደ ኤርትራዊው ስዊድናዊ አጥቂ አሌክሳንደር... read more
ምላሽ ይስጡ