ሚያዚያ 16 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተጠባቂው ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ከአገር ውስጥ ባለፈ የውጭ ታዛቢዎች የሚሳተፉበት መሆኑ ተመልክቷል።
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንደገለጹት፤ በዚህ ምርጫ ላይ ከአገር ውስጥ በተጨማሪ የውጭ አካላት ታዛቢ ይሆናሉ። ለማሳያነትም እንደ ኢጋድ እና የአፍሪካ ህብረት ያሉ ተቋማት እንደሚሳተፉና የመጀመሪያ ዙር ዳሰሳ ጥናት ማድረጋቸውን አስረድተዋል።
በሌላ በኩል በዚህ ምርጫ ላይ 37 የሚሆኑ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ፈቃድ ያገኙ ሲሆን፤ 1 ሺህ 1 መቶ 31 የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችም በምርጫው ሂደት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።
የመራጮች ምዝገባና የካርድ መውሰድ ሂደት ከቀናት በፊት መጠናቀቁ የሚታወስ ነው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ