ግንቦት 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰውን ልጅ ወደ ማርስ እና ጨረቃ ለማጓጓዝ እንዲሁም በህዋ ላይ በቋሚነት ለማስፈር ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍ የተሻገረበት አስገራሚ ሙከራ ተደረገ። የቻይና ሳይንቲስቶች የሰው ልጅ በህዋ ላይ መባዛት (Human Reproduction) የሚችል መሆኑን እና አለመሆኑን በጥልቀት ለማጥናት በጥናት ላይ የተመሰረቱ ሰው ሰራሽ የሰው ልጅ ሽሎችን (Artificial Embryo Models) ወደ ቲያንጎንግ የጠፈር ጣቢያ ልከዋል።
ከግንድ ሴል (Stem Cell) የተሰሩት እነዚህ የሽል ሞዴሎች የሰው ልጅ ከተረገዘ ከ14 እስከ 21 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚያሳየውን እጅግ የመጀመሪያ ደረጃ የዕድገት ሂደት ሙሉ በሙሉ መኮረጅ የሚችሉ ናቸው። ሆኖም ግን እነዚህ ሞዴሎች ወደ እውነተኛ የሰው ልጅ ፅንስ ወይም ሙሉ ሰውነት ሊያድጉ የማይችሉ በመሆናቸው ምንም ዓይነት የስነ-ምግባር ጥያቄ እንደማያስነሱ ተመራማሪዎቹ አረጋግጠዋል።
ሳይንቲስቶቹ በዚህ ሙከራ በህዋ ላይ ያለው አነስተኛ የስበት ኃይል እና የኮስሚክ ጨረራ በሰው ልጅ የሴል ዕድገት፣ በጂን መገለጫዎች እና በውስጥ አካላት አወቃቀር ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለማወቅ ፈልገዋል።
ይህ ታሪካዊ ሙከራ ወደ ጠፈር የተላከው በቅርቡ በተኮሰችው ቲያንዙ-10 (Tianzhou-10) በተባለችው የጭነት መንኮራኩር አማካኝነት ሲሆን፣ ሙከራው እየተመራ ያለው በቻይና የሳይንስ አካዳሚ የስነ-ሕይወት ተቋም (Chinese Academy of Sciences’ Institute of Zoology) አማካኝነት ነው።
ሳይንቲስቶች እንዳረጋገጡት ይህ ሽል በህዋ ላይ እንዴት እንደሚንቀሳቀስና እንደሚያድግ የሚታወቅበት ሚስጥር፣ የሰውን ልጅ ወደፊት በጠፈር ጣቢያዎች ወይም በሌሎች ፕላኔቶች ላይ በቋሚነት ለማስፈርና አዳዲስ ቅኝ ግዛቶችን ለመመስረት ለሚደረገው ጉዞ እጅግ ወሳኝና የመጨረሻው ቁልፍ መረጃ ሆኖ ያገለግላል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የሽግግር መንግስት ጥያቄና ኢ-ህገ መንግስታዊነት…
🔰ከኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ጋር የተደረገ ልዩ ቆይታ
https://youtu.be/ppufL2H7EWM
read more
የውጭ ምንዛሬ ተመን መጨመር በዶሮና እንቁላል ዋጋ ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ ተገለጸ
ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በ2017 በጀት አመት በዶሮና እንቁላል ምርት ላይ ለተስተዋለው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የውጭ ምንዛሬ መጨመር የራሱን... read more
የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት እና የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ
በመካከለኛው ምስራቅ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ከሰሞኑ የተፈጠረው ከፍተኛ ውጥረት የአለምን የድፍድፍ ነዳጅ ገበያ በእጅጉ አንቀጥቅጧል። እነዚህ ግጭቶች ወደ ሰፊ... read more
ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት 55,000ሜ/ቶን ዳፕ የተሰኘ የአፈር ማዳበሪያ የጫነችው MV DIONISIS የተባለችው 20ኛዋ መርከብ ጅቡቲ ወደብ ደርሳ የማራገፍ ኦፕሬሽን መጀመሯ ተገለጸ
ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚሆን 2.4 ሚለዮን ሜትሪክ ቶን ወይም 24,000,000( ሃያ-አራት ሚሊዮን) ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ገዝቶ ወደ አገር ውስጥ... read more
ከውጪ ሀገር ዜጋ ላይ የስርቆት ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ
ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 2 ሰዓት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9... read more
የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ማህበረሰቡ የሚቀላቀሉ ታጣቂዎች ቁጥር ቢጨምርም፣ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ እገታና ዘረፋዎች ስጋት መፍጠራቸው ተገለጸ
ሚያዚያ 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአማራ ክልል መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ መደበኛ ሕይወታቸው የሚመለሱ ታጣቂዎች ቁጥር እየጨመረ ቢሆንም፣ አሁንም... read more
የንስር ዓይን አስገራሚ ሚስጥር
👉ከ10ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ መሬት ላይ ያለውን ጉንዳን መመልከት ይቻላል ተብሏል
ነሐሴ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ንስር በአለም ላይ ካሉት ፍጥረታት... read more
ከቁጥጥር ውጪ የሆነው የኢራን ጦርነት፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀውሱን ለማረጋጋት የሚያደርጉት ጥረት ከሽፏል?
ሰኔ 01 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዩናይትድ ስቴትስ፣ በታሪክ ትልቁ የተባለውና በኦፕሬሽን “ኤፒክ ፉሪ” (Operation Epic Fury) የጀመረው የኢራን ጦርነት፣ ከፕሬዝዳንት... read more
የአርበኞች ቀንና የኋላ ታሪካቸው
👉
https://youtu.be/8PGo7h-L6zU
read more
የማሳጅ ቤቶች ስራ እና የነዋሪው ቅሬታ
👉
https://youtu.be/Ergmq7Iigxw
read more
ምላሽ ይስጡ