ግንቦት 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ በተለያዩ ግዛቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፉ የመጡት የሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) መረጃ ማዕከላት በአቅራቢያቸው በሚኖሩ ነዋሪዎች ላይ አስከፊ የአካል እና የስነ-ልቦና ጤና እክል እያስከተሉ መሆኑ ይፋ ሆኗል። ማዕከላቱን በማንቀሳቀስ ላይ ከሚገኙት ግዙፍ ወታደራዊ መሰል ማሽነሪዎች የሚወጣው ድምፅ አልባ ንዝረት ለአካባቢው ማህበረሰብ ታላቅ ስጋት ሆኗል።
በማዕከላቱ አቅራቢያ የሚኖሩ በርካታ ዜጎች በየቀኑ ከፍተኛ የሆነ ራስ ምታት፣ ማዞር፣ የማቅለሽለሽ ስሜት፣ የጆሮ ውስጥ ጩኸት እና ከእቅልፍ እጥረት ጋር የተያያዙ ከባድ የጤና ችግሮች እያጋጠሟቸው መሆኑን በምሬት እየገለጹ ይገኛሉ።
ለዚህ ቀውስ ዋነኛው መንስኤ ከማዕከላቱ የሚወጣው “ኢንፍራሳውንድ” (Infrasound) የተባለው እጅግ ዝቅተኛ ድግግሞሽ ያለው የድምፅ ንዝረት መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን፣ ይህ ንዝረት ከተለመደው የሰው ልጅ የመስማት አቅም በታች በመሆኑ በተራ የድምፅ መለኪያ መሣሪያዎች ላይ ሳይመዘገብ ሙሉ በሙሉ ጸጥተኛ መስሎ የሰውን አካል ግን በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳ ነው ተብሏል።
እነዚህ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት ሰርቨሮችን ለማቀዝቀዝ የሚያገለግሉ የኢንዱስትሪ ማራገቢያዎችን፣ ተርባይኖችን እና ግዙፍ የናፍጣ ጄነሬተሮችን በቀን 24 ሰዓት ያለ ምንም ማቋረጥ ያንቀሳቅሳሉ። ይህ ቀጣይነት ያለው ውህድ ንዝረት በአካባቢው ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ የሚገኝ ሲሆን፣ አዳዲስ የሰው ሰራሽ አስተዋጽኦ ማዕከላት ግንባታ ወደ መኖሪያ መንደሮች እየተጠጋ መምጣቱ ህዝቡን ክፉኛ አስቆጥቷል።
ከአሰቃቂው የድምፅ እና የንዝረት ብክለት በተጨማሪ እነዚህ ማዕከላት የሚበሉት የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን፣ ለቅዝቃዜ የሚጨርሱት በሚሊዮን የሚቆጠር ጋሎን የከርሰ ምድር ውሃ እና የሚያስከትሉት የአየር ብክለት በአሜሪካውያን ዘንድ ተከታታይ የሰላማዊ ሰልፍ እና የቅሬታ ድምፆች እንዲበራከቱ ምክንያት ሆኗል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በአፍሪካ ያለው የትምህርት ደረጃ የ21ኛውን ክፍለዘመን ደረጃና ፍላጎት እንደማይመጥን ተገለጸ
በአፍሪካ ያለው የትምህርት ደረጃ 21ኛውን ክፍለዘመን የሚመጥን አይደለም ሲሉ በ38ኛው የመሪዎች ጉባኤ ትይዩ መድረክ ላይ ገልጸዋል። ትምህርት በአፍሪካ ከሚጠበቀው በታች... read more
የTwitter ተባባሪ መስራች ጃክ ዶርሲ ያለ ኢንተርኔት የሚሰራ የመልዕክት መላኪያ መተግበሪያ “Bitchat”ን ይፋ አደረገ
ሐምሌ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የTwitter ተባባሪ መስራች የሆኑት ጃክ ዶርሲ (Jack Dorsey) ኢንተርኔት ሳያስፈልገው የሚሰራ አዲስ የመልዕክት መላኪያ መተግበሪያ "Bitchat"ን... read more
በህንጻዎች ላይ የእሳት ማጥፊያ መሳሪያ የማያሟሉ ተቋማትን ተጠያቂ የሚያደርግ መመሪያ ጸድቆ ወደ ስራ መገባቱ ተገለጸ
ኅዳር 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በመዲናዋ በሚከሰቱ ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች የሰዎችን... read more
በማርበርግ በሽታ ከተያዙ 11 ሰዎች ውስጥ 6ቱ በበሽታው ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ
ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከህዳር 5/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የማርበርግ ህክምና ምርመራ ሲደረግ የቆየ ሲሆን በበሽታው ከተጠቁ 11 ሰዎች... read more
ግዙፍ የሆኑ የከተማዋ ሞሎች እና ሪል-ስቴቶች የአከራይ ተከራይ ግብር እየከፈሉ አለመሆኑን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ
ታኅሳስ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በከተማዋ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግዙፍ ህንጻ የሚያከራዩ እና ሪል-ስቴት ባለቤቶች የአከራይ ተከራይ ግብር እንዲከፍሉ... read more
የኢትዮጵያ ሚዲያ ዳሰሳ፡ በነፃነት፣ በኢኮኖሚ እና በፀጥታ ተግዳሮቶች መካከል
ሙሉ ዘገባውን ለመስማት ሊንኩን ይጫኑ
በተጠናቀቀው የበጀት አመት መገናኛ ብዙሃን መረጃ ለህዝቡ በተለያዩ አማራጮች ከማሻገር ባለፈ የነበራቸው አዎንታዊ እና አሉታዊ ሚና... read more
ኢራን ከአምስት ቀናት በኋላ የተወሰኑ የስልክ ጥሪ አገልግሎቶችን መፍቀድ ጀመረች
ጥር 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢራን ለሁለት ሳምንታት የቀጠለውን መጠነ ሰፊ ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት ጥሎት የነበረውን የኮሙኒኬሽን እገዳ በከፊል ማንሳቱ ተገለጸ።... read more
ሊቨርፑል ፊቱን ወደ ጎንዛሎ ኢናሲዮ በማዞር ይህን ፖርቹጋላዊ የመሀል ተከላካይ ለማስፈረም እንቅስቃሴ መጀመሩን የሚጠቁሙ መረጃዎች ወጡ
ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሊቨርፑል በዚህ ክረምት የተከላካይ መስመሩን ማጠናከር ዋነኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አድርጎ ወደ ዝውውር ገበያው ለመግባት... read more
ኢትዮጵያ በግጭት አካባቢ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ጥበቃ እንዲደረግ የሚያዘውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንጋጌ እንድትቀበል ግፊት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
ኢትዮጵያ በግጭት አካባቢ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ጥበቃ እንዲደረግ የሚያዘውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንጋጌ እንድትቀበል ግፊት እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር... read more
አንዶኒ ኢራዮላ ቀጣዩ የሊቨርፑል አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
ግንቦት 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአምና ሻምፒዮኖቹ ሊቨርፑሎች ዘንድሮ ካሳለፉት ደካማ የውድድር ዘመን አንፃር ባለፈው ቅዳሜ አሰልጣኝ አርን ስሎትን ካሰናበቱ... read more
ምላሽ ይስጡ