ሚያዚያ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በባህር ኃይል የጦር መርከብ ላይ በመገኘት፣ አዳዲስ የክሩዝ እና ፀረ-መርከብ ሚሳይል ሙከራዎችን በበላይነት መርተዋል። ይህ ጥቃት የማድረስ አቅምን የመፈተሽ እርምጃ፣ ፒዮንግያንግ በባህር ላይ ያላትን ወታደራዊ የበላይነት ለማሳየት የወሰደችው ወሳኝ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።
በሙከራው ወቅት ሚሳይሎቹ በባህር ላይ የተቀመጡ ኢላማዎችን በከፍተኛ ጥንቃቄ የመምታት ብቃታቸውን ያሳዩ ሲሆን፣ መሪው ኪም ጆንግ ኡንም በውጤቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። መሪው አክለውም የሀገሪቱን ባህር ኃይል በዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ማጠናከር ለሉዓላዊነት መከበር አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።
ይህ ድንገተኛ የጦር መሳሪያ ሙከራ በኮሪያ ልሳነ ምድር ያለውን ውጥረት ይበልጥ ያባባሰው ሲሆን፣ ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል። የሰሜን ኮሪያ የባህር ኃይል አቅም መጎልበት በቀጣናው ባለው የጂኦ-ፖለቲካዊ ሚዛን ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችልም ወታደራዊ ተንታኞች ትኩረት ሰጥተውታል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ