ሰኔ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት “ሰላም፣ ዴሞክራሲ እና ልማት በትግራይ፡ እድሎች እና ፈተናዎች” በሚል ርዕስ በሴንተር ፎር ሬስፖንሲብል ኤንድ ፒስፉል ፖለቲክስ (Centre for Responsible and Peaceful Politics) በተዘጋጀው መድረክ ላይ ነው።
በዚሁ መድረክ አሁን ላይ ለትግራይ ህዝብ ሰላም ቅንጦት ሆኗል ብለዋል።
አቶ ጌታቸው አክለውም፣ በትግራይ ውስጥ ባሉ ጥቂት ኃላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች የሚራመደው የፖለቲካ አስተሳሰብ የትግራይ ህዝብ የህልውና አደጋ እንዲጋረጥበት አድርጓል ሲሉ አክለዋል።
ምንም እንኳን ለረጅም ጊዜያት በትግራይ ሰላም፣ ዴሞክራሲ እና ልማት ላይ የምክክር መድረኮች ተካሂደው ሀሳቦች ቢንሸራሸሩም፣ አሁን ከምንጊዜውም በላይ ሰላም ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ይህ መድረክ በመቀሌ ከተማ ቢዘጋጅ ደግሞ የተሻለ ነበር ያሉት ሚኒስትሩ፣ የፖለቲካ መዋቅሩ ኃላፊነት ሊኖረው እንደሚገባም አሳስበዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ