ሰኔ 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ለአካባቢ ብክለት የሚዳርጉ እና አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ ምርቶች በሥነ ምህዳር ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ለመከላከል አዋጁን ማዉጣት ማስፈለጉ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡
አዋጁ በምክር ቤት የተለያዩ ሃሳቦች እንዲንሸራሸሩም ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ አሁን በተገለጸዉ መረጃ መሰረት የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ 300 ሺሕ የሚጠጉ ዜጎችን ስራ አጥ የሚያደርግ በመሆኑ በድጋሚ ሊታይ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡
የፕላስቲክ ምርት ማምረት ከተቋርጠ ሀገሪቱ እስከ 50 ቢሊዮን ብር በላይ ሊያሳጣት እንደሚችል የኢትዮጵያ ፕላስቲክና ጎማ አምራቾች የዘርፍ ማህበር ገልጿል፡፡
አዋጁ በከተማዋ ከ800 በላይ በፕላስቲክ ምርት ላይ የተሰማሩ አምራቾችን ስጋት ላይ የጣለ መሆኑን የገለጸው ማህበሩ መንግስት ተግባራዊ ከመደረጉ አስቀድሞ ሊያጤነው ይገባል ብሏል።
አዋጁ በግልጽ የተቀመጠ ነገር የሌለውና የብዙዎችን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑም ተመላክቷል፡፡
የፕላስቲክ አምራቾች ደረጃውን የጠበቀ ምርት እንዲያመርቱ ማድረግ እንጂ ከዘርፉ እንዲወጡ ሊደረግ እንደማይገባ ተገልጿል።
አዋጁን ተከትሎ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ እንዲሁም አሁን በምርት ላይ ያሉ ፋብሪካዎች ሽያጭ ማቆማቸውን የተገለጸ ሲሆን ይህ በሀገር ላይ ትልቅ ኪሳራ የሚያመጣ ጭምር መሆኑን ማህበሩ ገልጿል።
በመሆኑም የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ተግባራዊ ከመሆኑ አስቀድሞ ሊፈተሽ እንደሚገባ ማህበሩ አስገንዝቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ