የተሟላ መረጃ በመመዝገብ አስፈላጊውን ጥናት የሚያደርግ አህጉራዊ ግብረ ሃይል በማቋቋም ለስደተኞች ዘላቂ መፍትሄ በመፍጠር ከሃገራት ጋር መረጃ ለመለዋወጥ እንደሚረዳ ተገልጿል።
አፍሪካ የስደተኞችን አሃዛዊ መረጃ የሚያጠና ግብረ ሃይል ማቋቋም ከስደትኞች አስተዳደር ጋር ያለውን ነባራዊ የፋይናንስ እጥረት ችግር ለይቶ ለስደተኞች ተስማሚ ሁኔታ ለመፍጠር ጉልህ ሚና ሊኖረው እንደሚችል የስደተኞች እና ተመላሽ አገልግሎት ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጿል።
በአለም አቀፍ ደረጃ ስደተኞችን በሚመለከት የወጡ ህጎችን ተፈጻሚ ከማድረግ አንጻር አሃዛዊ መረጃዎችን የሚያቀርብ እና አጠቃላይ ሁኔታዎችን የሚያጠና ጠንካራ ተቋም እንደ አህጉር ማቋቋሙ ተገቢ መሆኑን የስደተኞች እና ተመላሽ አገልግሎት የፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ደመቀ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያም ስደተኞችን ተቀብላ እንደምታስተናግድ ሃገር አሃዛዊ መረጃዎች በጥናት የተደገፉ መሆናቸው ስደተኞች የሚያጋጥማቸውን ማህበራዊ እና አስተዳደራዊ ችግሮች ይቀርፋል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ቀደም ባሉት ጊዚያት በስደተኞች ዙሪያ ሰፊ ስራዎችን ስትሰራ እንደቆየች የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ አህጉራዊ ጠንካራ ግብረሃይል መቋቋሙ በዘር ያለውን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚረዳ አመላክተዋል።
በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች የሚፈልሱ ስደተኞችን አሃዛዊ ተጨባጭ መረጃዎች በጥናት በማስደገፍ በአህጉር ደረጃ ያለውን የስደተኞች አያያዝ ችግር እና የፋይናንስ እጥረት የመፍታት አቅም እንደሚኖረው ነው የስደተኞች እና ተመላሽ አገልግሎት የፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ደመቀ ገልጸዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ