ዛሬ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ውስጥ ወደ በረራ ይዞ መግባት ከሚከለከሉ ቁሳቁሶች መካከል ከመንገደኞች የሚሰበሰብ የሲጋራ መለኮሻ (ላይተር) ጊዜያዊ የማስቀመጫ ስፍራ ውስጥ ጭስ በመከሰቱ ለመንገደኞች ደህንነት ሲባል ሕንፃው ለጊዜው አገልግሎት መቋረጡን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡
በመሆኑም በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎች የምትጓዙ መንገደኞች በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራችሁ እንድትሳፈሩ ሲል አሳስቧል፡፡
ከነገ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለመደው የሀገር ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት እንደሚቀጥል አስታውቆ፤ ለተፈጠረው መጉላላት መንገደኞቻችንን ይቅርታ ጠይቋል፡፡
ምላሽ ይስጡ