ለመሆኑ ከሰሃራ በታች ያሉት ሃገራት እነማን ናቸው?
ጥቅምት 19 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ በአየር ኃይል አቅሟ “ከሰሃራ በታች አገራት ቀዳሚ” የሚያደርጓትን ዘመናዊ የጦር ጀቶች መረከቧን ይፋ አድርጋለች።
ይህ ታሪካዊ ክስተት የአገሪቱን የመከላከል እና የሰማይ ላይ ጥበቃ አቅም ወደ አዲስ ከፍተኛ ምዕራፍ ያሸጋገረ ሲሆን፣ በክልሉ ያለውን የደህንነት እና የጂኦፖለቲካ ሚዛንም በእጅጉ የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።
ነገር ግን ከዚህ አየር ኃይልን ካጠናከረ አጋጣሚ ጀርባ ብዙዎች የሚያነሱት ጥያቄ አለ፡
ለመሆኑ «ከሰሃራ በታች ያሉት አገራት» የሚባሉት እነማን ናቸው?
«ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት» ምንድን ናቸው?
በዓለም አቀፍ ደረጃ እና በጂኦግራፊያዊ ምደባ «ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት» (Sub-Saharan Africa) የሚለው ጽንሰ-ሐሳብ የሚያመላክተው ከሰሃራ ታላቅ በረሃ በስተደቡብ የሚገኙትን የአፍሪካ አገራት ነው።
ይህ ምደባ በሰሜን አፍሪካ ከሚገኙት እንደ ግብፅ፣ አልጄሪያ፣ ሊቢያ፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ እና ሱዳን ካሉት አገራት ውጭ ያሉትን 48 ያህል አገራት ያጠቃልላል።
🔰በስራቸው የሚገኙ ዋና ዋና ቀጠናዎች እና አገራት፡
👉ምሥራቅ አፍሪካ፡ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ጅቡቲ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ማዳጋስካር እና ሌሎችም።
👉ምዕራብ አፍሪካ፡ ናይጄሪያ፣ ጋና፣ ሴኔጋል፣ ማሊ፣ ኮት ዲዕቮር (አይቮሪ ኮስት)፣ ላይቤሪያ፣ ሲራሊዮን፣ ጊኒ እና ሌሎችም።
👉መካከለኛው አፍሪካ፡ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC)፣ ካሜሩን፣ ቻድ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ጋቦን እና ሌሎችም።
👉ደቡባዊ አፍሪካ፡ ደቡብ አፍሪካ፣ አንጎላ፣ ሞዛምቢክ፣ ዚምባብዌ፣ ዛምቢያ፣ ቦትስዋና፣ ናሚቢያ፣ ሌሶቶ እና ሌሎችም።
ኢትዮጵያ በዚህ ሰፊ እና በርካታ አገራትን በያዘው ቀጠና ውስጥ የቴክኖሎጂ ብልጫ ያላቸውን የጦር ጀቶች መታጠቃዋ፣ በአቪዬሽን ወታደራዊ ዘርፍ የነበራትን ቀዳሚነት ይበልጥ ያጠናከረና የአገሪቱን ሉዓላዊነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስከበር ትልቅ መተማመንን የፈጠረ ሆኗል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ