መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ከዛሬ ከመስከረም 15/2019 ጀምሮ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ከተማ ማሽከርከር እንደተከለከለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ። አንዳንድ ወንጀል ፈጻሚዎች ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም የቅሚያ እና የስርቆት ወንጀል ሲፈጽሙ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን መምሪያው ገልጻል። ወንጀል ፈጻሚዎች ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር እና የተሰረቁ እቃዎችን ለማጓጓዝ ሞተር ብስክሌትን በብዛት እንደሚጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንቡን እንደማያከብሩ በተለይ ቀይ መብራትን መጣስ፣ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም በአሽከርካሪዎቹ በስፋት የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መሆናቸውን የፖሊስ መረጃ አመላክቷል። ወንጀልን ለመከላከል እና በሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የሚፈጸምን የደንብ ጥሰት ለመቆጣጠር ከዛሬ ከመስከረም 15/2019 ዓ/ም ጀምሮ ከኮድ 4 እና ከፖሊስ ሞተር ብስክሌት ውጭ በአዲስ አበባ ከተማ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች እና ባለ ንብረቶች ህጉን እንዲያከብሩ ያሳሰበው ፖሊስ ማሳሳቢያውን በሚተላለፉት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጻል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ለመጪው አዲስ ዓመት ከ700 ሺሕ ኩንታል በላይ ቀይ ሽንኩርት ለገበያ ሊቀርብ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ2019 አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚፈጠረውን የኅብረተሰቡን ከፍተኛ መሠረታዊ ፍጆታ ምርቶች ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል... read more
ድጋፍ የሚሹት በጎ አድራጎት ድርጅቶች..👉
https://youtu.be/eMP3cELi4bk
read more
በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ የሥነ ጽሑፍ፣ ትምህርትና የአስተዳደር ስርዓት ውስጥ ዱካቸውን ካስቀመጡት ምሁራኖች መሀል ከፍ ብለው እናገኛቸዋለን። እውቀታቸውን ለሀገራቸውና ለወገናቻው የቻሉትን አጋርተው፡ ያልተናገሩትን ደግሞ በመጽሃፋቸው ከትበው ያለፉትን የአለቃ ታዬ ገብረ ማርያም አስደናቂ የሕይወት ዘመን ቆይታቸውን እና ሥራዎቻቸውን ያድምጡ! 👉
https://youtu.be/pLH7fF2MaOM
read more
ሞርተን ዩልማንድ አትሌቲኮን ለመቀላቀል መስማማቱ ተዘግቧል።
ሐምሌ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአትሌቲኮ ማድሪድ ክለብ የፖርቹጋሉን ስፖርቲንግ ሊዝበን አምበል እና የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን አማካኝ ሞርተን ዩልማንድን ለማስፈረም የተቃረበ... read more
የአረንጓዴ አሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያና አሥተዳደር አዋጅ ጸደቀ
ታኅሳስ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ አመት የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ ከአለም... read more
ከሕገ-ወጥ ደላሎች “ፈጣን ወጥመድ” ወደ ሕጋዊው የሥራ ስምሪት ከለላ፦ አዲሱ የአንድ ማዕከል አገልግሎትና የቴክኖሎጂ አማራጮች
በኢትዮጵያ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የተሻለ የሥራ ዕድል ፍለጋ ወደ ውጭ ሀገራት የሚንቀሳቀሱ ቢሆንም፣ አብዛኛዎቹ በሕገ-ወጥ ደላሎች ሐሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ተታልለው... read more
ለ2/3ኛው የአለም ሙቀት መጨመር ተጠያቂ የሆኑት 10 በመቶ የሚሆኑ አለም ላይ ያሉ ሃብታሞች እንደሆኑ ተመራማሪዎች ገልጸዋል
ሀብታሞች የሚጠቀሙበት እና ኢንቨስት የሚያደርጉበት መንገድ የሙቀት ማዕበል እና የድርቅ አደጋን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አድርጓል ሲሉ ተመራማሪዎች የአየር ንብረት... read more
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 41ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር ጋር ለኢትዮጵያ ዘመናዊ የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የ53,300,000.00 ኤስ.ዲ.አር... read more
የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅም ያሳድጋል የተባለው የኢትዮጵያ – አውሮፓ ህብረት የንግድ ፎረም 2026 ተጀመረ
ሚያዚያ 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅም ያሳድጋል የተባለውና ከዛሬ ሚያዝያ 12 እስከ ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚቆየው የኢትዮጵያ... read more
🐠 ጾታቸውን እንደፈለጉ የሚቀይሩት አስገራሚዎቹ የባህር ዓሳዎች! 🌊
ሰኔ 10 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዱር እንስሳትና በባህር ስነ-ህይወት ዓለም ውስጥ እጅግ አስገራሚ እና ውስብስብ ከሚባሉ የመራቢያ ስልቶች መካከል አንዱ... read more
ምላሽ ይስጡ