መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚው በአቶ አንዋር አብራር በኩል ባወጣው ይፋዊ የሚዲያ መግለጫ፣ ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ባከናወነው ሰፊ ሥራ በጉራጌ ዞን በእኖር እና እዣ ወረዳዎች የሚገኙ 19 የገጠር መንደሮችን በበዓሉ ዋዜማ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል። ቀድሞም ቢሆን በደማቅ የመስቀል በዓል አከባበሩ የሚታወቀው አካባቢው፣ አሁን ደግሞ በእነዚህ መንደሮች ኤሌክትሪክ መግበቡ የበዓሉን አከባበር ይበልጥ ያሳምረዋል ተብሏል። ይህን የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ለማከናወን ከ132 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ ለሥራው ስኬትም 25.92 ኪሎ ሜትር መካከለኛ እና 38 ኪሎ ሜትር ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ተከናውኗል። በፕሮጀክቱ 2 ሺህ 295 የሚጠጉ ቆጣሪዎች የተገጠሙ ሲሆን፣ በአንድ ቆጣሪ አማካይ 5 የቤተሰብ አባላት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ በተሰላው መሠረት 11 ሺህ 475 ዜጎችን የመብራት ባለቤት ማድረግ ተችሏል። በተጨማሪም ከወጣው አጠቃላይ ወጪ ውስጥ 40 ሚሊዮን የሚሆነው በሕብረተሰቡ ቀጥተኛ ተሳትፎና የባለቤትነት ስሜት የተሸፈነ መሆኑ የሕዝብና የተቋሙን አብሮነት ድንቅ ማሳያ እንደሆነ ተገልጿል። ይህ የልማት ሥራ የአካባቢውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በማነቃቃትና በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና ከመጫወቱም በላይ፣ የዘንድሮውን የመስቀል በዓል ለነዋሪዎቹ ልዩ እንደሚያደርገው ይጠበቃል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ
አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ።
ሀገረ ስብከቱ... read more
ከአህጉሪቱ ወሳኝ የ2063 አጀንዳዎች ሁሉ ሰላምና ጸጥታ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው ተባለ
ከአህጉሪቱ ወሳኝ የ2063 አጀንዳዎች ሁሉ ሰላምና ጸጥታ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው ሲሉ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ አዲሱ የህብረቱ ሊቀመንበር ጃኦ... read more
በአደገኛ ጦር ተወግታ የ100 አመት እድሜ ያስቆጠረች ዓሣ ነባሪ
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአላስካ አዳኞች በተያዘችው ዓሣ ነባሪ ላይ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተሰራ የጦር ጫፍ መገኘቱ ሳይንቲስቶችን አስገርሟል።
ይህ... read more
የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ከሶማሊያ እንዲወጣ የመጠየቁ ጉዳይ እና አንደምታው…
የባህር በር እና የውሃ ጉዳይ ለሀገራት የምጣኔ ሃብት ጉልበት በመሆናቸው ሀገራት ሲራኮቱበት ይስተዋላል። ኢትዮጵያ የባህር በር ከሌላቸው ሀገራት መካከል ብትሆንም... read more
የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የኢ- ሰርቪስ አገልግሎት ማስጀመሩን አስታወቀ
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥራት ያለው፣ ቀልጣፋና ምቹ የሆነ አገልግሎትን ለመስጠትና እንደ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በቂ የህግ ጥበቃ ለማድረግ የኢ- ሰርቪስ... read more
ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ በሚንቀሳቀሱ የቀይ መስቀል አባላት እና ንብረት ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አካላት ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ ተጠየቀ
ታኅሳስ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቀይ መስቀል ማህበር ከተቋቋመበት ከ1927 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎች እና የልማት ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ... read more
81 በመቶ የሚሆኑ የንግድ ባንክ ደንበኞች የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለ
ታኅሳስ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባንኩ ዲጂታል ፋይናንስን ለማስፋፋት ካቀደው እቅድ ቀድሞ ማሳካት መቻሉን አመላክቷል፡፡
የዲጂታል ስርዓቱ መስፋፋት በአገልግሎት አሰጣጥ ሒደት... read more
ከወላጅነት መብትና ቀለብ አወሳሰን ጋር በተገናኘ የኢ-መደበኛ የገቢ ምንጭ ያላቸዉ ወላጆች ገቢን ለማወቅና ለማስፈጸም አለመቻሉ ስራዉን ፈታኝ እንዳደረገዉ ተጠቆመ
ነሐሴ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከወላጅነት መብት እና ቀለብ አወሳሰን ጋር በተያያዘ ጉዳያቸው በፍ/ቤት የሚታይ ህጻናት ሙሉ መብታቸው የተጠበቀ እንዲሆን በወጣው... read more
በሰባ ቦሩ ወረዳ በአፈር መደርመስ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል
በጉጂ ዞን ሳባ ቦሩ ወረዳ በባሕላዊ መንገድ ማዕድን በማውጣት ላይ የነበሩ 8 ሰዎች በአፈር መደርመስ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡
አደጋው ትናንት... read more
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር እየተዘጋጀሁ ነው አለ
ኅዳር 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማርና ሌሎች ተግባራትን በላቀ ደረጃ ለመፈፀምና ተወዳዳሪነቱን ለማስቀጠል ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ... read more
ምላሽ ይስጡ