መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ዘንድሮ እጅግ በጣም አስደናቂ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው የብሉግራናዎቹ አምበል እና የፊት መስመር ተጫዋች ብራዚላዊው ራፊኛ በስፖቲፋይ ካምፕ ኑ እስከ 2030 የሚያቆየውን ውል ለመፈረም መስማማቱን የክለቡ ቴክኒካል ዳይሬክተር ዴኮ አሳውቋል። የስፔኑ ሀያል ክለብ ባርሴሎና ብራዚላዊውን የክንፍ መስመር ተጫዋች ራፊኛን በክለቡ እስከ ሰኔ 2030 የሚያቆየውን አዲስ የውል ማራዘሚያ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሱን የክለቡ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ዴኮ በይፋ አረጋግጧል። በክለቡ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተናገረው ዴኮ፣ የ29 ዓመቱ ተጫዋች አሁን ያለውን ውል በሁለት ተጨማሪ ዓመታት የሚያራዝምበት ድርድር ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁንና ጥቂት የወረቀት ስራዎች ብቻ መቅረታቸውን ገልጿል። ራፊኛ በያዝነው አዲሱ የ2026/27 የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ ሃንሲ ፍሊክ ታክቲክ ውስጥ የቡድኑ ዋና የውጤት መሪ እና ወሳኝ ተጫዋች መሆን ችሏል። ብራዚላዊው ኮከብ በተለዋዋጭ የመሃል እና የክንፍ ማጥቃት ቦታዎች ላይ በመሰለፍ በአስደናቂ ብቃት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በላሊጋው ባደረጋቸው የመጀመሪያ ስድስት ጨዋታዎች ብቻ ዘጠኝ ግቦችን በማስቆጠር አስደናቂ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል። ባርሴሎና በአዲሱ የውድድር ዘመን ባደረጋቸው 7 ጨዋታዎች ሁሉንም በማሸነፍ በ21 ነጥብ ሊጉን እየመራ ሲሆን፣ 24 ንጹህ ግብ ያለው አስደናቂ የማጥቃት እንቅስቃሴ እንዲኖረው የራፊኛ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን መናገር ይቻላል። ሃንሲ ፍሊክ ለተጫዋቹ የሰጡት ነፃነት እና የቡድኑ ዋና ተጽዕኖ ፈጣሪ የፊት መስመር መሪ ማድረጋቸው ለቡድኑ ውጤታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። በተጨማሪም ዴኮ ክለቡ የወደፊት ተስፋ የሆኑትን ወጣት ተጫዋቾች የማርክ በርናልን እና የዣቪ ኤስፓርት ውል ከራፊኛ ጎን ለጎን የሚያራዝም መሆኑን አስታውቋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ፍራንክ ጄምስ ላምፓርድ እና ማይክል ካሪክ የፕሪሚየር ሊጉ ከአሰልጣኝነት የመሰናበት እጣ ፋንታ የተደቀነባቸው 2 አሰልጣኞች መሆናቸው ተገልጿል
መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ውድድር ዘመን ከተጀመረ አራት ሳምንት ወይም 40 ጨዋታዎች የተደረገ ቢሆንም፣ የእንግሊዝ የስፖርታዊ... read more
የሱፐር ሊግ ምስረታ 96 ቡድኖች የሚሳተፉበት Unify league በሚል አዲስ የውድድር መድረክ ለማዘጋጀት በማሰብ ጥያቄያቸውን ለUEFA እና FIFA ስለማስገባታቸው ተገልጿል
ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሱፐር ሊግ በ2021 ሚያዝያ ወር ላይ ሀሳቡ ከተጠነሰሰ በኋላ በርካታ ክለቦች ይህንን ሱፐር ሊግ ተቀላቅለው... read more
ሊቨርፑል – ከቶተንሃም
♻️በመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 በቀጥታ ይከታተሉ፡፡
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ወደ ለንደን አቅንቶ ቶተንሃምን ይገጥማል።
ይህንን ጫዋታ ስፖርት... read more
ስንብትን አልፈራም ሲል ፔፕ ጋርዲዮላ ሀሳቡን ሰጥቷል
ከዛሬው ተጠባቂ የሻምፒዮንስ ሊግ የknock out Play-off ጨዋታዎች በፊት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሰጠው የቅድመ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የትኛው ማንቸስተር... read more
የእንግሊዝ ክለቦችን የሚያፋጥጠው የዩሮፓ ሊጉ የፍፃሜ ጨዋታ ዳሰሳ
በክለቦች የውድድር መድረክ ላይ ሁለተኛ እርከን የሚሰጠው የዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በሁለት እጅግ አስከፊ የውድድር ዘመንን ባሳለፉ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች... read more
የሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ዳሰሳ
በየአመቱ ከሚከናወኑ እና የክለቦች ፉክክር ከሚደምቅበት እንዲሁም በአውሮፓ ውስጥ ሀያሉ ክለብ ለመባል የሚደረግ የክለቦች ትንቅንቅ በተለያዩ የአውሮፓ ግዙፍ ስቴዲየሞች በባውዛ... read more
ቡካዮ ሳካ የሻምፒዮንስ ሊግ የሳምንቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተሰይሟል
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጥቁሩ ፈርጥ ባሳለፍነው እሮብ በነበረው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ6ኛ ዙር ጨዋታ ሞኒኮ ላይ 2 ጎል... read more
ቶፑሪያ የቀላል ሚዛን የቀበቶ ባለቤት መሆን ቻለ
menahriafm | አለማችን ላይ አሉ የሚባሉ እጅግ ምርጥ እና አጓጊ ፍልሚያዎችን በማዘጋጀት የሚታወቀው UFC አይን በማያስከድኑ ፍልሚያዎች ይዞ ትላንት ሲመለስ... read more
ሊቨርፑል ሚሎሽ ኬርኬዝን ሁለተኛ ፈራሚያቸው ለማድረግ ተቃርበዋል
ይሄ ሀንጋሪአዊ በ2023 ሰኔ ወር ላይ በርንማውዝን ከተቀላቀለ በኋላ በጣም አስደናቂ የግል አቅሙን እያስመለከተ ይገኛል። በዛ ላይ ገና 20 አመቱ... read more
ጀማል ሙሲያላ የጀርመን ብሄራዊ ቡድን የወንዶች ምርጡ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለባየር ሙኒክ እየተጫወተ የሚገኘው ጀማል ሙሲያላ 56 በመቶ ድምጽ በማግኘት ነው የአመቱ ምርጥ የጀርመን ብሄራዊ... read more
ምላሽ ይስጡ