መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኤሊኖን ለዘመናት በተለያየ ስያሜ እየተጠራ አሉታዊ ተጽዕኖ ሲያሳድር የቆየ አለም አቀፍ ክስተት እንደሆነ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የስትራቴጂክና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አይድሩስ ሀሰን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሜትሪዮሎጂ ኢንስቲትዮት በሰጠው የትንበያ መረጃ፣ በአገሪቱ በ8 ክልሎች፣ በ37 ዞኖች፣ በ178 ወረዳዎች የኤሊኖን ክስተት እንደሚያጋጥም መገለጹን አስታውሰዋል። ዘንድሮ በተከሰተው ኤሊኖን ሁለት ከፍተኛ ተጽዕኖዎች ማለትም ከፍተኛ የዝናብ እጥረት ወይም ድርቅ እና የጎርፍ አደጋ እንደሚጠበቅ ምክትል ኮምሽነሩ አመላክተዋል። ኮምሽኑ ከሌሎች የመንግስት ተቋማት ጋር በመሆን ለክስተቱ ብቻ ሳይሆን ከኤሊኖን ባሻገር ምላሽ ለመስጠት በቂ ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል። ክስተቱን ተከትሎ ለሚያጋጥም አደጋ ምላሽ ለመስጠት የሰብዓዊ እርዳታን በራስ አቅም ለመሸፈን ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በሰጡት አቅጣጫ መሰረት በተጀመረው “የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” ትልቅ አቅም መፍጠር እንደተቻለ አመላክተዋል። በዚህም መሰረት እንደ አገር ለኤሊኖን ብቻ ሳይሆን፣ ከኤሊኖን ባሻገር ለሚያጋጥም አደጋ ምላሽ ለመስጠት በቂ ዝግጅት እንደተደረገ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የስትራቴጂክና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አይድሩስ ሀሰን አስታውቀዋል። ኮምሽኑ ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ጋር በጋራ ባዘጋጀው መድረክ ለፌደራል እና የክልል የኮምዩኒኬሽን እና ሚዲያ አካላት በኤሊኖን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት እና በተቀናጀ የሚዲያ እና መረጃ ልውውጥ ዙሪያ ምክክር እያደረገ ነው። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ለፖለቲካ ፓርቲዎች የማስጠንቀቂያ እግድ መነሳቱ ለቀጣዩ ምርጫ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገለጸ
ታኅሳስ 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከጠቅላላ ጉባዔ፣ ከኦዲትና በሴት አባላት ቁጥር አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋር... read more
የመሬት መንቀጥቀጥ እና የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ባለባቸው አካባቢዎች ለተለያየ ጉዳይ የሚያቀኑ ግለሰቦች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ተጠቆመ
ጥር 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) እሳተ ገሞራና የመሬት መንቀጥቀጥን የመሳሰሉ ድንገተኛ የተፈጥሮ አደጋዎችን ሁነት በምስል ለማስቀረት እና ለመመልከት ወደ ስፍራው... read more
ለ57ሺህ ታዳጊ ወጣቶች የክረምት የስፖርት ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ለ57ሺህ ታዳጊ ወጣቶች የክረምት የስፖርት ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ... read more
የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል የሚሰጠውን የ3.3 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ዕርዳታ ለማገድ በቀረበው ታሪካዊ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ሊመክር ነው
ሰኔ 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል የሚሰጠውን የ3.3 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ዕርዳታ ሙሉ በሙሉ ለማገድ በቀረበው አዲስ... read more
መምህራንን የቤት ባለቤት ለማድረግ የማደራጀት ስራ እየሰራ መሆኑን ማህበሩ አስታወቀ
መምህራንን የቤት ባለቤት ለማድረግ የማደራጀት ስራ እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
የቤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ... read more
የቱሪዝም ሚኒስቴር ለ38ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ በሚደረገው ቅድመ ዝግጅት በ15 ሆቴሎች የድንገተኛ ፍተሻ ማድረጉ ተገለጸ
ጥር 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 38ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ የቱሪዝም... read more
ተሽከርካሪዎችን የሰረቁ ግለሰቦች እስከ 10 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ
ሶስት የቀድሞ ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ተሽከርካሪዎችን በመስረቅ ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ተቀጡ።
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት... read more
ቻይናውያን ሳይንቲስቶች በሰው ሰራሽ ማህፀን አማካኝነት ህጻናትን የሚወልድ የመጀመሪያውን “ሮቦት” እየሰሩ መሆኑ ተገለጸ
ጥር 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የቻይና ሳይንቲስቶች በዓለም የመጀመሪያ የሆነውንና ፅንስን በሰው ሰራሽ ማህፀን ውስጥ ተሸክሞ በሰላም መገላገል የሚችል የእርግዝና ሮቦት... read more
የቴሌ ሲስተም በመጠቀም ከግለሰብ አካውንት 238,000ብር የሰረቀች የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኛ ተያዘች
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቴሌ ሲስተምን በመጠቀም ከግለሰብ አካውንት ብር የሰረቀች የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሏን የሶዶ... read more
ባለፉት ስምንት ወራት ለ20 ሚሊየን ዜጎች የወባ ምርመራ ተደርጎላቸዉ 8.2 ሚሊየን የሚሆኑት በደማቸዉ ዉስጥ ወባ መገኘቱ ተገለጸ
አለም አቀፉ የወባ ቀን የፊታችን ሚያዝያ 17 ቀን 2017 በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ኹነቶች እንደሚከበር በተገለጸበት የጤና ሚኒስቴር መግለጫ ላይ የጤና... read more
ምላሽ ይስጡ