መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዩኒቨርሲቲው ቀደም ሲል በአንድ የሜጀር ዘርፍ ብቻ ሲሰጥ የነበረውን ሥልጠና በማሻሻል ተማሪዎች በሁለት ተያያዥ የትምህርት ዓይነቶች እንዲሰለጥኑ የሚያስችል የደብል ዲግሪ ፕሮግራም ማዘጋጀቱን አስታውቋል። ሥርዓቱ የሠልጣኞችን አቅም ለማሳደግና በተለያዩ የትምህርት መስኮች የሚፈለገውን የሰው ኃይል ለማሟላት የሚያግዝ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የሥራ ላይ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ቆንዳሌ ለጣቢያችን ገልጸዋል። እስካሁን ባለው የትምህርት አሰጣጥ አንድ ተማሪ አንድ የትምህርት ዘርፍ ብቻ ይወስድ እንደነበር በመጥቀስ፤ አሁን ላይ ሁለተኛ የትምህርት ዓይነት በመማር በሜጀር እና በማይነር መከታተል እንደሚችሉ አብራርተዋል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ብቸኛው የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ ጥራት ያለው እና ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በመግለጽ፤ በዚህ የትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች ተመርቀው ሲወጡ ከሁለቱ ዲግሪዎች በአንዱ ሥራ ለማግኘት እንዲችሉ የሚረዳቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ በዘንድሮ የትምህርት ዘመን አዳዲስና የተሻሻሉ የአካዳሚክ ፕሮግራሞችን ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል፡፡ በ2019 የትምህርት ዘመን የተዘጋጁት አዳዲስ ፕሮግራሞች ተማሪዎች የእውቀት ደረጃቸውን ለማሻሻል፣ የሙያ አማራጫቸውን ለማስፋት እና የተሟላ ክህሎት ለማዳበር የሚረዷቸው መሆኑ ተመልክቷል፡:
___
ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
ምላሽ ይስጡ