መስከረም 04 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ)በ1868 ዓ.ም. በመቅደላ ዘመቻ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎንደር አካባቢ እንደተዘረፈ የሚነገርለት አጼ ቴዎድሮስ ይጠቀሙት የነበረ መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ቅርስ አሰባሳቢ ግለሰብ ለሽያጭ መቅረቡን የታሪክ ተመራማሪው አሉላ ፓንክረስት (ዶ/ር ) ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። ከአንድ ሳምንት በኋላ በአቡ ዳቢ ከተማ ለሽያጭ የሚቀርበውን ቅርስ መንግሥት በድርድር ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በሕግ ቅርሱን ለመመለስ የሚያስችል አሁናዊ ሁኔታ ባለመኖሩ አስቸጋሪ ሁኔታ እንደገጠማቸው አስረድተዋል። ቅርሱን ለመመለስ ኢትዮጵያውያን በብዙኃን መገናኛና በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ ንቅናቄ መፍጠር እንደሚገባቸው ጠቁመው፣ መንግሥትም የዲፕሎማሲ አካሄዱን ማጠናከር እንደሚገባው አሳስበዋል። ባለሀብቶች እና ዲያስፖራውም በጨረታው በመሳተፍ ቅርሱ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለስ ሚናቸውን እንዲወጡ ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት ጥሪ አቅርበዋል። ቅርሱን በጨረታ ለመሸጥ 250 ሺህ ዩሮ መነሻ ቀርቧል።
___
ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
ምላሽ ይስጡ