ሐምሌ 30 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ኢኳዶር፣ ባባሆዮ በተባለች ከተማ የሚገኘው ማርቲን ኢካዛ ሆስፒታል ሰኔ 9 ቀን 2015 ዓ.ም አንድ ያልተለመደና አሳዛኝ ክስተት አስተናግዷል። እድሜያቸው 76 የሆኑት አያት ቤላ ሞንቶያ በጽኑ ታመው ወደ ሆስፒታሉ ከገቡ በኋላ፣ በወቅቱ በነበሩት ሀኪሞች “ህይወታቸው አልፏል” የሚል ኦፊሴላዊ የሞት ምስክር ወረቀት ተሰጣቸው።
የሞታቸውን ዜና የሰሙት ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው የቀብር ስነ-ስርዓታቸውን ለመፈጸም አስከሬኑን በሬሳ ሳጥን ውስጥ አድርገው ወደ ቀብር ማዘጋጃ ቤት ወሰዱት። ለሰዓታት ያህል የሀዘን ስነ-ስርዓት ሲካሄድ ቆይቶ፣ ከቀብሩ በፊት የሬሳ ሳጥኑን ከፍተው ልብሳቸውን ለመቀየር ሲዘጋጁ ግን ያልተጠበቀ ድንጋጤ ተከሰተ።
የአያት ቤላ ሞንቶያ ልጅ የሆነው ጊልበርት ባልቤራን እንደተናገረው፣ ከሰዓታት ሀዘን በኋላ ከሳጥኑ ውስጥ ደካማ ማንኳኳትና የመተንፈስ ድምፅ መሰማት ጀመረ። ቤተሰቦቻቸው ሳጥኑን በፍጥነት ሲከፍቱ፣ አያት በህይወት ሆነው ግራ እጃቸውን በማንቀሳቀስና አፋቸውን በመክፈት አየር ለማግኘት ሲታገሉ ተመለከቱ።
ይህ ክስተት በወቅቱ በሆስፒታሉ ባለሙያዎች ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥን የፈጠረ ሲሆን፣ አያት ወዲያውኑ ወደ ጽኑ ህክምና ክፍል ተመልሰው ኦክስጅን እንዲያገኙ ተደረገ። የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት አያት የካታሌፕሲ (Catalepsy) ተብሎ በሚጠራ የነርቭ መታወክ ሁኔታ ውስጥ ወድቀው የነበረ ሲሆን፣ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያለ ሰው የልብ ምቱና የመተንፈስ ፍጥነቱ እጅግ አነስተኛ ከመሆኑ የተነሳ እንደ ሞተ ሰው ተቆጥሮ በስህተት ሊደመደም ይችላል።
ክስተቱን ተከተሎ የኢኳዶር ጤና ሚኒስቴር አያት በስህተት ሞተዋል ተብለው የሞት ምስክር ወረቀት እንዴት ሊሰጣቸው እንደቻለ ለማጣራት ብሔራዊ ኮሚቴ አቋቁሞ ምርመራ ጀምሮ ነበር።
ሆኖም ግን፣ አያት ቤላ ሞንቶያ በጽኑ ህክምና ክፍል ውስጥ ለአንድ ሳምንት ያህል ከቆዩ በኋላ ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም በተከሰተ የstroke ችግር ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ በይፋ ተረጋግጧል።
የመጀመሪያው አጋጣሚ ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ በህክምና ታሪክ ውስጥ እጅግ አስገራሚና በማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ መነጋገሪያ ከሆኑ ክስተቶች አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ኢራን ከአምስት ቀናት በኋላ የተወሰኑ የስልክ ጥሪ አገልግሎቶችን መፍቀድ ጀመረች
ጥር 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢራን ለሁለት ሳምንታት የቀጠለውን መጠነ ሰፊ ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት ጥሎት የነበረውን የኮሙኒኬሽን እገዳ በከፊል ማንሳቱ ተገለጸ።... read more
በጦርነት ቀጠናዎች ለመለየት አስቸጋሪ የሆኑትን የፕላስቲክ ፈንጂዎች በቀላሉ የሚያጋልጠው አዲስ ድሮን ተሰራ
ሐምሌ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአሜሪካው ቢንግሃምተን ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተመራማሪዎች፣ በተለምዶ “ቢራቢሮ” እየተባሉ የሚጠሩትን እና በብረታ ብረት መመርመሪያዎች ለመለየት እጅግ አስቸጋሪ... read more
በመዲናዋ መዝናኛ ቦታዎች የሚሰሩ ሰራተኞች ቅሬታ
https://youtu.be/en9ekzIubDw
read more
አውስትራሊያ ያረጁ ጎማዎችን ወደ ባቡር ሀዲድ አስደንጋጭ መምጠጫ በመቀየር የጥገና ወጪን እየቀነሰች ነው ተባለ
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አውስትራሊያ የባቡር ሀዲድ ጥገና ወጪን ለመቀነስ እና የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ የሚያስችል አዲስ ዘዴ ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን... read more
‘‘በደብረጽዮን የሚመራው ህወሓት ከኤርትራ መንግስት ጋር እየሰራ ነው’’ – ጊዜያዊ አስተዳደሩ
የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራር ከሆኑት ከአቶ #ጣዕመ #አረዶም ጋር የተደረገ ቆይታ
https://youtu.be/F1ilWPpFztU
read more
ከገቢ ግብር፣ ታክስና ቀረጥ ጋር ተያይዞ በ2016 በጀት አመት ወደ 309.8 ሚሊዮን ብር ሳይሰበሰብ መቅረቱ ተገለፀ
ሰኔ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2016 የበጀት ዓመት የፋይናንስ ህጋዊነት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት በዛሬው እለት ለህዝብ... read more
የዶናልድ ትራምፕ በዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ላይ እየጨመረ ያለው ጫና
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪን በሩሲያ ላይ የሚደረገውን ጦርነት በተመለከተ ጫና... read more
ሚዲያዎች በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን የመረጃ ፍሰት በሰላማዊ መንገድ በማስተዳደር ለህዝቡና ለሃገሪቱ የሚበጁ ዘገባዎችን በሃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በፖለቲካዊ ሁኔታዋ ላይ እያለፈች ባለችው ወሳኝ ጊዜ ሚዲያዎች በሃላፊነት እና በተጠያቂነት መረጃ ማቅረብ እንዳለባቸው ምሁራን ለመናኸሪያ ሬዲዮ... read more
የብሔር ተኮር የፌዴራሊዝም ስርዓቱ ምን ያህል የብሔር ብሔረሰቦችን መብት አስጠብቋል?
በሀገራችን ኢትዮጵያ የዜጎች አኗኗር ከቀን ወደ ቀን መልክ እና ሁኔታ እየቀያየረና እየተባባሰ ስለምጣቱ በርካታ ማሳያዎች አሉ። ለዚህም በምክንያትነት የሚነሳው የብሔር... read more
በእንጨት ብስክሌት የሰራው ኢትዮጵያዊ ወጣት እያነጋገረ ነው
👉1,255 ኪሎ ሜትር በዩኬ አቋርጦ እየተጓዘ ነው ተብሏል
መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ከተማ የሚገኘው የኢምፔሪያል ኮሌጅ ተማሪ... read more
ምላሽ ይስጡ