ሐምሌ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአትሌቲኮ ማድሪድ ክለብ የፖርቹጋሉን ስፖርቲንግ ሊዝበን አምበል እና የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን አማካኝ ሞርተን ዩልማንድን ለማስፈረም የተቃረበ ሲሆን፣ በግል ጥቅማጥቅሞች ዙሪያ ከተጫዋቹ ጋር ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሷል።
ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ ማትዮ ሞሬቶ እንደዘገበው፤ አትሌቲኮ ማድሪድ ከሊዝበን ጋር የነበረው የ35 ሚሊዮን ዩሮ የመጀመሪያ ጥያቄ ውድቅ ከተደረገበት በኋላ፣ አጠቃላይ የዝውውር ሂሳቡን ወደ 40 ሚሊዮን ዩሮ (35 ሚሊዮን ቋሚ እና 5 ሚሊዮን ዩሮ ተጨማሪ ማበረታቻዎች) በማሳደግ ተጫዋቹን ለማስፈረም ተቃርቧል።
የ26 ዓመቱ አማካኝ እስከ 2031 ዓ.ም የሚያቆየውን የ5 ዓመት ኮንትራት ለመፈረም የተስማማ ሲሆን፣ በአዲሱ ክለቡ የቅድመ-ውድድር ዝግጅት ለመጀመር ወደ ማድሪድ ያመራል ተብሎ ይጠበቃል። አትሌቲኮ ማድሪድ ፊቱን ወደ ዩልማንድ ያዞረው፣ ከዎልቭሱ ጆአኦ ጎሜስ ወኪል ጆርጅ ሜንዴስ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ተከትሎ የዝውውር እቅዱን በመቀየሩ ነው።
ሞርተን ዩልማንድ ባለፈው የ2025/2026 የውድድር ዘመን በፖርቹጋል ፕሪሜራ ሊጋ እና በተለያዩ ውድድሮች ለስፖርቲንግ ሊዝበን በአማካኝ መስመር ላይ ቁልፍ ሚና የነበረው ሲሆን፣ 1 ግብ አስቆጥሮ 1 ለግብ የሚሆን ኳስ ማመቻቸት ችሏል።
አትሌቲኮ ማድሪድ ይህንን ተጫዋች አጥብቆ የፈለገበት ዋነኛው ምክንያት በአሰልጣኝ ዲዬጎ ሲሚዮኒ የጨዋታ ስልት ውስጥ ጠንካራ፣ ኳስ አስጣይ እና መከላከል ላይ ያተኮረ ንቁ የተከላካይ አማካኝ (Defensive Midfielder) እንዲሁም በተከላካይ እና በአጥቂ መስመር መካከል ድልድይ የሚሆን ተጫዋች ስለሚያስፈልገው ነው።
ዩልማንድ በስፖርቲንግ ሊዝበን መሪነቱን እና የአማካኝ ክፍሉን በአግባቡ የመቆጣጠር ብቃቱን ያሳየ በመሆኑ፣ ሲሚዮኒ ለሚገነቡት አዲስ የአማካኝ መስመር ጥንካሬ ዋነኛ ምርጫቸው አድርገውታል፤ ተጫዋቹም በሮጂብላንኮዎቹ ቤት ለ5 ዓመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የዓለምን ቀልብ የሳበው የሰሜን ኮሪያ የባህር ላይ ወታደራዊ ጉልበት ትርኢት
ሚያዚያ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በባህር ኃይል የጦር መርከብ ላይ በመገኘት፣ አዳዲስ የክሩዝ እና... read more
የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር የእስራኤል አትሌቶች ከዓለም አቀፍ ውድድሮች እንዲታገዱ ጠየቁ
መስከረም 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ፣ በእስራኤል አትሌቶች ላይ የዓለም አቀፍ እገዳ እንዲጣል ጥሪ ማቅረባቸው ተገለጸ።... read more
ሀሰተኛ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን ሲመነዝሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራ መሆኑን የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለጸ
ሐምሌ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ዮርዳኖስ ዓለምሰገድ፣ ሄዋን ግደይ እና እስከዳር ወሰን የተባሉ ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12... read more
በሶስት ምዕራፍ ለ325 ሺሕ ተዋጊዎች የተሃድሶ ስልጠና እንደሚሰጥ ተገለጸ
ኅዳር 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመጀመሪያ ዙር ለ75ሺሕ፤ በሁለተኛው ምዕራፍ 1መቶ ሺሕ፤ በሶስተኛው ዙር ደግሞ 150 ሺሕ ተዋጊዎች ተሃድሶ እንደሚሰጥ... read more
ጀርመን ሙሉ በሙሉ በሃይድሮጂን ኃይል የሚሰራ የባቡር መርከቦችን ስራ አስጀመረች
ሰኔ 23 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)ጀርመን በዓለም የመጀመሪያውን ሙሉ በሙሉ በሃይድሮጂን ኃይል የሚሰራ የባቡር መርከቦችን በማስጀመር በአረንጓዴ ትራንስፖርት አብዮት ግንባር... read more
የበጀት ውስንነትና የጸጥታ ችግር ለሰባተኛው አገራዊ ምርጫ በሚፈለገው ልክ እንዳንቀሳቀስ አድርጎናል ሲሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ገለጹ
መጋቢት 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሌላ በኩል አስቻይ ሁኔታ ባለባቸው አካባቢዎች ማህበረሰቡን ለማንቃት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን ቪዥን ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ... read more
ለሚዲያ ባለሙያዎች በሃገር አቀፍ ደረጃ አንድ ወጥ መታወቂያ ሊዘጋጅ ነው ተባለ
ለሚዲያ ባለሙያዎች በሃገር አቀፍ ደረጃ ዓለም ዓቀፍ የሙያ ምስክርነትን የሚያረጋግጥ አንድ ወጥ መታወቂያ ሊዘጋጅ መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት... read more
በከተማዋ ላይ የታይሮይድ መድሃኒት ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመሆኑ አሳስቦናል ሲሉ ተጠቃሚዎች ገለጹ
ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለመናኸሪያ ሬዲዮ ቅሬታቸውን ያቀረቡት የእንቅርት መድሃኒት (ታይሮክሲን) ተጠቃሚ መድሃኒቱን የመንግስት መድሃኒት መሸጫ በሆነው ከነማ መደብር... read more
ተመራማሪዎች በአንድ ሳምንት ውስጥ ፀጉርን ሙሉ ለሙሉ የሚያበቅል አዲስ ሞለኪውል ማግኘታቸውን አስታወቁ
👉እስከዛሬ ጥቅም ላይ ከሚውሉት መካከል የአሁኑ ግኝት እጅግ የተለየና ፈጣን ለውጥን የሚያሳይ ነው ተብሎለታል
ሐምሌ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከፀጉር መርገፍ ጋር... read more
በመሬት የይዞታ ማረጋገጥ ስራ ላይ ለሚነሱ ችግሮች በወረቀት ያለው ሰነድ ህጋዊ ሆኖ እንደሚቀርብ ተገለጸ
ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የመሬት ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ላይ በዲጅታልና በወረቀት ሆኖ በሚቀርብበት ወቅት የሚፈጠሩ ቅሬታዎችና ክፍተቶች ካሉ... read more
ምላሽ ይስጡ