ሐምሌ 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በስፔን ሀገር የሚኖር አንድ የ60 ዓመት አዛውንት፣ ከቀን ወደ ቀን እየበረታ የመጣ የራስ ምታት ሕመም እና ድንገተኛ የባሕርይ መለዋወጥ ስላስቸገረው ወደ ሕክምና ክሊኒክ ያመራል።
የመጀመሪያ ደረጃ የጭንቅላት ኤክስሬይ (Brain Scan) ውጤቱ ሐኪሞቹን ክፉኛ አስደነገጠ። በአእምሮው ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የተበተኑ እብጠቶች (Lesions) የታዩ ሲሆን፥ ይሄም በትክክል የመጨረሻ ደረጃ ላይ የደረሰና የተስፋፋ የአንጎል ካንሰር (Metastatic Cancer) ይመስል ነበር። ሆኖም ግን ሐኪሞቹ በሰውነቱ ውስጥ የካንሰሩ መነሻ የሆነ የመጀመሪያ እጢ (Primary Tumor) የትም ቦታ ሊያገኙ አልቻሉም።
ጉዳዩ ግራ ያጋባቸው የሕክምና ባለሙያዎች ይበልጥ ጥራት ያለውና የላቀ የኤምአርአይ (Higher-resolution MRI) ምርመራ እንዲያደርግ አዘዙ። ውጤቱም ፍጹም ያልተጠበቀ ሆነ! እብጠቶቹ ካንሰር ሳይሆኑ በአእምሮ ቲሹዎች ላይ የተበተኑ በፈሳሽ የተሞሉ ትናንሽ ከረጢቶች ነበሩ። ከዚህም በላይ በከረጢቶቹ ውስጥ የዓማካይ (Pork Tapeworm) ትል ራሶችን በግልጽ ማየት ተቻለ።
ይህ የሕክምና ሁኔታ “ኒውሮሲስቲሰርኮሲስ” (Neurocysticercosis) በመባል ይታወቃል። በሽታው የሚከሰተው አንድ ሰው በተበከለ ምግብ፣ ውሃ ወይም ባልታጠበ እጅ አማካኝነት በአይን የማይታዩ የትል እንቁላሎችን በአጋጣሚ በሚውጥበት ጊዜ ነው። እነዚህ እንቁላሎች በአንጀት ውስጥ ከፈለፈሉ በኋላ የሆድ ዕቃን ግድግዳ በጥሰው በመውጣት፣ ከደም ዝውውር ጋር ቀጥታ ወደ አእምሮ ይጓዛሉ።
እዚያም አእምሮ ጥልቀት ባለው ክፍል ውስጥ በመቀመጥ ትናንሽ የፈሳሽ ከረጢቶችን (Cysts) ይሠራሉ። ለዓመታትም ያለምንም ምልክት ፍጹም ተደብቀው መኖር ይችላሉ ነው የተባለው።
የሰውነታችን የበሽታ መከላከያ ሥርዓት በመጨረሻ ትሎቹን አግኝቶ ማጥቃት ሲጀምር የሚፈጠረው ከፍተኛ የአእምሮ መቆጣትና እብጠት (Inflammation)፣ በኤክስሬይ ላይ በትክክል ጠንከር ያለ የጭንቅላት ካንሰር ገጽታን ይይዛል።
እነዚህ ከረጢቶች ባረፉበት የአእምሮ ክፍል ላይ በመመስረትም በሽተኛው ለከፍተኛ የሚጥል በሽታ (Seizures)፣ ለስትሮክ ወይም ለአእምሮ መዛባት ሊዳረግ ይችላል ነው የተባለው።
ሐኪሞቹ ትሎቹን ለመግደል ጠንከር ያሉ የፀረ-ፓራሳይት መድኃኒቶችን የሰጡት ሲሆን፥ ትሎቹ በሚሞቱበት ጊዜ አእምሮው በአደገኛ ሁኔታ እንዳያብጥ ለመከላከል ከፍተኛ መጠን ካላቸው ስቴሮይዶች ጋር አደባልቀው ሰጥተውታል። አዛውንቱም ሙሉ በሙሉ ከበሽታው ሊያገግም ችሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ