ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ማንቸስተር ዩናይትድ የቶተንሃሙን አምበል ክሪስቲያን ሮሜሮን ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ እያዘጋጀ መሆኑ ተዘግቧል።
የ28 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ተከላካይ ቶተንሃም በፕሪሚየር ሊጉ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት 17ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ተከትሎ፣ በዚህ ክረምት ክለቡን ይለቃል ተብሎ በስፋት ይጠበቃል። አርጀንቲናዊው ጋዜጠኛ ጋስተን ኤዱል እንደዘገበው፤ ማንቸስተር ዩናይትድ ቀጣዩ የተጫዋቹ ማረፊያ ለመሆን ተስፋ በማድረግ ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ይገኛል።
ጊቭሚስፖርት (GiveMeSport) በበኩሉ፣ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ሮሜሮን አሁንም የቡድኑ ወሳኝ አካል አድርጎ ስለሚመለከተው በቀላሉ አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑን ገልጿል። የ2022 የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ሮሜሮ፣ ክለቡ ቶተንሃም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም እንኳ ራሱን በፕሪሚየር ሊጉ ካሉ ምርጥ የመሀል ተከላካዮች አንዱ ማድረግ በመቻሉ፣ ቶተንሃሞች ለዝውውሩ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን እንደሚጠይቁ ይገመታል።
የትራይባል ፉትቦል (Tribal Football) ዘጋቢው አሌክስ ሮበርትስ በበኩሉ፤ ሮሜሮ በቶተንሃም ያለው የኮንትራት ውል ማፍረሻ 50 ሚሊዮን ዩሮ መሆኑንና ይህንን ገንዘብ ለማቅረብ ዩናይትድ ዝግጁ መሆኑን ገልጾ፤ ተጫዋቹን ከአገሩ ልጅና ከቅርብ ጓደኛው ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ጋር የማጣመር ዕቅድ እንዳላቸው ዘግቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ኢትዮጵያ የወሰደችው ከናይጄሪያ ነዳጅ የማስመጣት አማራጭ ረጅም ርቀትና ከፍተኛ ወጪ የምታወጣበት ቢሆንም፣ ዓለም አቀፉን ጫና ለመቋቋም ይረዳል ተባለ
ሰኔ 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ሀገሪቱ ከውጭ የምታስገባውን የነዳጅ ምርት የማጓጓዝ ሥራ ከ40 ዓመታት በኋላ... read more
ከአድዋ ድል ባሻገር….
https://youtu.be/gJFVVdYp7R4
read more
በፀሐይ ኃይል የሚሞላ የቴስላ መኪና
👉የፈጠራ ስራ ወይስ የሩቅ ህልም?
ሐምሌ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አንድ ግለሰብ የኤሌክትሪክ መኪናውን ቴስላ ሞዴል 3ን በፀሐይ ኃይል በመሙላት የቴክኖሎጂ አዲስ... read more
“አንድም ሰው በሕይወት አይተርፍም!” — ኢራን ለአሜሪካ ያስተላለፈችው የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ
መጋቢት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመካከለኛው ምስራቅ ለዓመታት ሲንተከተክ የቆየው ፍጥጫ አሁን ወደማይመለስበት እና እጅግ አደገኛ ወደሆነው ቀጥተኛ ጦርነት ምዕራፍ... read more
ከምንጊዜውም በላይ ሰላምን ለማጽናት የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
ህዳር 01 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት የሚቀጥፍ፣ ብዙሃኑን ለመፈናቀልና ለጥቃት የሚዳርገውን ጦርነት ማስቆም የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን... read more
በአማራ ክልል ባለዉ የጸጥታ ችግር ምክንያት አምስት ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸው ተገለጸ
በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት በ2017 ዓ.ም በሶስት ዙር የተማሪዎች ምዝገባ የተካሄደ ሲሆን በተካሄደው ምዝገባም ከሰባት ሚሊዬን በላይ ተማሪዎችን... read more
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 41ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር ጋር ለኢትዮጵያ ዘመናዊ የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የ53,300,000.00 ኤስ.ዲ.አር... read more
በተፈናቃዮች ስም የሚሰራ ፖለቲካ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ እያደረገው ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከእንደራሴዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት መድረክ፣ በተፈናቃዮች ላይ የሚሰራ ፖለቲካ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ እንቅፋት... read more
እንግሊዝ እና አሜሪካ የኑክሌር ኃይል ፕሮጀክቶችን ለማፋጠን የሚያስችል ስምምነት ሊፈራረሙ ነው
መስከረም 05 ቀን (መናኸሪያ ሬዲዮ) ዩናይትድ ኪንግደም እና ዩናይትድ ስቴትስ በአትላንቲክ ውቅያኖስ በሁለቱም በኩል የኑክሌር ኃይል ማመንጫዎችን ግንባታ የሚያፋጥን ታሪካዊ... read more
በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚስተዋሉ ጥቃቶችን ለመከላከል ከህጉ ባለፈ ማህበረሰቡን የሚያነቃ ስራ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ
ኅዳር 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የነጭ ሪቫን (የጸረ-ጾታዊ ጥቃት) ቀን በሀገራችን ኢትዮጵያ ለ19ኛ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ... read more
ምላሽ ይስጡ