ሰኔ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከአሁን በፊት “ሰበበር ኤነዌ” እና “ሟን ያትገፍሬ” በተሰኙት ሁለት የጉራጌኛ አልበሞቹ እንዲሁም በተለየ መልኩ “እያ ኧረሙድን ጉራጌነተና” በተሰኘው ዜማው ትልቅ አድናቆተና ተቀባይነትን ያተረፈው ወጣቱ የጉራጌኛ ድምፃዊ፣ የዜማና የግጥም ደራሲ አርቲስት አምደ-ገብርኤል አድማሱ “ወሄነት” የተሰኘ አዲስ አልበም የፊታችን እሁድ ሰኔ 22/10/2017 ዓ.ም በአማርድ ኢንተርቴይመንት የዩቲዩብ ቻናል ለአድማጮች ተደራሽ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
አልበሙ በአጠቃላይ 10 ዘፈኖችን የያዘ ሲሆን በግጥም እና ዜማ አምደ-ገብርኤል አድማሱ፣ አለማየሁ ወልዴ፣ አብራር ደሊልና ደሳለኝ ፍቃዱ የተሳትፉበት ሲሆን አልበሙን ለመስራት ሁለት ዓመታት ከስድስት ወራት የጊዜ ቆይታ አሳልፌለሁ ያለው ደግሞ ድምፃዊው አምደ-ገብርኤል አድማሱ ነው፡፡
በዓልበሙ የሙዚቃ ቅንብር የተሳተፉት መሀመድ ኑርሁሴን፣ ሮሆቦት ሺመልስና እና ያሬድ እንዳለ ሲሆኑ የአልበሙን ሚክሲንግ እና ማስተሪንጉ የሰራው ደግሞ መሀመድ ኑርሁሴን ነው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ