የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የአፍሪካ ህፃናት ቀንን ምክንያት በማድረግ ህፃናት ከፍተኛ ትኩረትን የሚሹ እንደመሆናቸው በቢሮ ደረጃ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
የአፍሪካ የህፃናት ቀን በደቡብ አፍሪካ በአፓርታይድ ጊዜ መብታቸው እንዲከበር የጠየቁ ህፃናት በግፍ የተጨፈጨፉበትን ክስተት ለማሰብ ቀኑ የሚከበር ሲሆን ኢትዮጵያም ይህንን ቀን ታከብራለች፡፡
ይህንን ቀን አስቦ ከማዋል ባለፈ የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በተለያዩ መንገዶች ህፃናት ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ለጣቢያችን የገለፁት የቢሮ ምክትል ሃላፊ እና የህፃናት ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ እመቤት ተስፋዬ ናቸው፡፡
በቀዳማይ ልጅነት ህፃናት እስከ 3 ዓመታቸው ድረስ የተመጣጠነ ምግብ እንዲመገቡ ከ3 ነጥብ 57 ሚሊየን ብር በላይ በጀት መድቦ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራ እንደሚገኝ እንዲሁም የመዝናኛ እና የህፃናት ማቆያ ስፍራዎችን ማስፋፋት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ህፃናት ትኩረት እና እንክብካቤን የሚሹ መሆናቸውን፣ በተለይም መብት እና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ቢሮው ከፍተኛ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ የገለፁት በቢሮው የህፃናት መብት እና ደህንነት ማስጠበቅ ዳይሬክተር አቶ እንዱአለም ታፈሰ ናቸው፡፡
ህፃናት ላይ መስራት ሀገር የሚረከቡ ዜጎችን መፍጠር ነው የሚሉት አቶ አንዱአለም ህፃናት ተኮር የሆኑ ተግባራትን ማከናወን ከተቋማት ባሻገር የማህበረሰቡ ሃላፊነት መሆኑን አንስተዋል፡፡
የአፍሪካ ህፃናት ቀን ታስቦ እንዲውል የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እ.ኤ.አ 1991 ውሳኔውን ያስተላለፈ ሲሆን ዘንድሮ በአፍሪካ ለ35ኛ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ34ኛ ጊዜ በዛሬው እለት ይከበራል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ