ዩኒሳ ላለፉት 20 ዓመታት ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርትና የሰው ኃይል አቅም ግንባታ ላይ ሲሠራ መቆየቱ በመርሐ ግብሩ ተገልጿል።
በዚህ ዓመት 58 የዶክትሬት ምሩቃንን ማስመረቁ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ዩኒቨርሲቲው በሀገሪቱ የሚያደርገውን የሰው ኃይል ግንባታ አመላካች ነው ተብሏል።
የዩኒሳ የሃያ ዓመት ጉዞ ጥራት ያለው የድኅረ ምረቃ ትምህርት ተደራሽነትን በማስፋት እና የምርምር አቅምን በማጠናከር፣ ብሎም በፈጠራ ሥራዎች ሀገራዊ ልማትን በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን አመላካች ነው ተብሏል።

የዩኒቨርሲቲው ቆይታ ከሰው ኃይል ግንባታ ባሻገር የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እንዲጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተመላክቷል።
አብዛኛዎቹ ምሩቃን በዩኒቨርሲቲዎች፣ በመንግሥት ተቋማት፣ በንግድ ዘርፎች፣ በኅብረተሰብ ጤና አገልግሎት እና በሌሎች አገልግሎቶች ላይ የሚገኙ መሆናቸው ተመላክቷል።
ምላሽ ይስጡ