🟢በኖርዌይ የምትገኘው ሎንግይርቢየን ከተማ ነዋሪዎቿ በከተማዋ እንዳይሞቱ እና እንዳይቀበሩ በሕግ መከልከሏ አነጋጋሪ ሆነ
ሕዳር 14 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሰሜን ዋልታ አቅራቢያ በኖርዌይ ስቫልባርድ ደሴት ላይ የምትገኘው ሎንግይርቢየን (Longyearbyen) ከተማ፣ ነዋሪዎቿ በከተማዋ እንዳይሞቱ እና አስከሬናቸው እንዳይቀበር የሚከለክል ሕግ ተግባራዊ ማድረጓ በዓለም አቀፍ ደረጃ አስገራሚ ሆኖ ቀጥሏል።
ይህ ያልተለመደ ሕግ የወጣበት ዋነኛ ምክንያት የአካባቢው የአየር ንብረት እጅግ በጣም ቀዝቃዛ ከመሆኑ የተነሳ መሬቱ ዓመቱን ሙሉ በበረዶ የታሰረ (Permafrost) በመሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት በከተማዋ የሚቀበሩ አስከሬኖች ስለማይፈርሱ፣ በውስጣቸው ያሉ አደገኛ ቫይረሶችና በሽታ አምጪ ተሕዋስያን ሳይሞቱ ለአስርት ዓመታት ሊቆዩ ይችላሉ።
ሳይንቲስቶች እ.ኤ.አ. በ1918 በዓለም ላይ ተከስቶ በነበረው የስፓኒሽ ፍሉ (Spanish Flu) ወረርሽኝ የሞቱ ሰዎችን አስከሬን በከተማዋ ቆፍረው ባወጡበት ወቅት፣ ቫይረሱ በበረዶው ውስጥ ሳይሞት በሕይወት መገኘቱ ለሕጉ መውጣት ዋነኛ መነሻ ሆኗል።
በዚህም መሠረት በከተማዋ የሚኖር ማንኛውም ሰው በጠና ሲታመም ወይም ዕድሜው ገፍቶ ለሞት ሲቃረብ፣ ወደ ሌላ የኖርዌይ ክፍል በአውሮፕላን ተወስዶ ቀሪ ጊዜውን እንዲያሳልፍ እና ሕይወቱ ሲያልፍም በዚያው እንዲቀበር ይደረጋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የመክፍል አቅም ለሌላቸው ዜጎች መንግስት ወጪያቸውን ሊሸፍንላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት አስታወቀ
ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ሁነው የመክፍል አቅም ለሌላቸው ዜጎች መንግስት ሙሉ ወጪያቸውን መሸፈን የሚችልበት አሰራር መዘጋጀቱን... read more
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በ2017 ዓ.ም ከቅጣት 404 ሚሊዮን ብር ገቢ ማሰባሰቡን አስታወቀ
ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከድርጅቶች፣ ከግለሰቦች እና ከመንግስት ተቋማት የተጣለባቸውን የቅጣት... read more
2018 ዓ.ም ከበጎ ፍቃደኞች መቅኔ መሰብሰብ እንደሚጀመር ተገለጸ
ሐምሌ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት በመጪው አመት መቅኔ መሰብሰብ ሊጀምር እንደሆነ አገልግሎቱ ለመናኸሪያ ሬድዮ... read more
የአሜሪካው ደግ ዳኛ በ88 አመታቸው ማረፋቸውን ተከትሎ የመንግስት ባንዲራዎች በግማሽ እንዲውለበለቡ ትዕዛዝ ተሰጠ
ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በፍርድ ቤት ባሳዩት ርህራሄና ቀልድ የተሞላበት ባህሪያቸው “የአሜሪካ ደግ ዳኛ” በመባል በዓለም ዙሪያ የሚታወቁት ተወዳጁ... read more
ሰበር ዜና | ሰሜን ኮሪያ ባህር ኃይሏን በኒውክሌር ታጥቃለች፤ ግዙፍ የጦር መርከቦችንም ትገነባለች ሲሉ ኪም ጆንግ ኡን አስታወቁ!
ሰኔ 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው የባህር ኃይል ክፍሏን በታክቲካል የኒውክሌር መሳሪዎች ለማስታጠቅ እና ይበልጥ... read more
ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉ ምግብና መጠጦችን እንዳስወገደ የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ
ኅዳር 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመዲናዋ 6 ሚሊየን 44ሺህ 402 ብር የሚያወጣ ግምት ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉ ምግብና መጠጦች ናቸው... read more
ኢትዮ ቴሌኮም በጅማ ከተማ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችል የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረመ
ኢትዮ ቴሌኮም ከጅማ ከተማ አስተዳደር ጋር በከተማዋ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያደርግ የስማርት ሲቲ “ስማርት ጅማ” ፕሮጀክትን ለመተግበር የሚያስችል... read more
የተፋሰሱ ሃገራት ኮሚሽን ሊቋቋም ባለበት ወቅት ግብጽ ወደ ናይል ትብብር መመለሷን ኢትዮጵያ በአጽዕኖት መከታተል አለባት ተባለ
የአባይ ውሃን በፍትሀዊነት እና በምክንያታዊነት ለመጠቀም ከ15 ዓመት በፊት የተቋቋመ የናይል ቤዚ ኢንሼቲቭ ህጋዊ ቢሆንም ግብፅ ውድቅ ማድረጓዋ እና የናይል... read more
በቢሾፍቱ ከተማ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ
መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ በመጪው እሁድ ለሚከበረው የሆራ አርሰዲ በዓል ወደ ከተማዋ የሚያቀኑ 10 ሚሊየን የሚጠጉ... read more
በትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ለማከናወን ከ22 ጊዜ በላይ ውይይት መደረጉ ተገለጸ
ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል አጀንዳ ለማሰባሰብ ክልሉን ወክለው ከሚንቀሳቀሱ ተቋማት ጋር ተደጋጋሚ ውይይት ቢደረግም፣ እስካሁን የሚፈለገው ውጤት... read more
ምላሽ ይስጡ